Connect with us

ይድረስ ለክቡር ከንቲባ

ይድረስ ለክቡር ከንቲባ
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

ይድረስ ለክቡር ከንቲባ

ይድረስ ለክቡር ከንቲባ
የሴይጣን ቤት ጉዳይ ዙሪያዎትን እንዲፈትሹ አንድ ምልክት ነው፡፡
ሄኖክ ስዩም በድሬቲዮብ

የሴጣን ቤት ይፈርስም ማለትዎን ሰማሁ፤ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔ እርስዎና መንግስትዎ ጸረ ቅርስ ናችሁ የሚል እምነት የለኝም፤፤ በጸረ ቅርስ፣ በአፍቃሪ ከርስ መታጀባችሁን ስጠቁም ግን ጠብሰቅ ያለ ማስረጃ በማቅረብ ነው፡፡

ሴጣን ቤት ባይፈርስ የምመኘው እትብቴ ስለተቀበረበት ሳይኾን የሀገሬ የሲኒማ ኢንዱስትሪ እትብት ስለተቀበረበት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሚመሯት ከተማ ብዙ ቅርሶች አሉ፡፡ አዲስ አበባ ዋና ከተማችን ብቻ ሳትኾን የባህውርታዊቷ ኢትዮጵያ የባህልና የትውፊት እንብርት ናት፡፡ ብዙ ቅርሶች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ከማይነግሩ የድል አጥቢያ አርበኞች ተከበዋል፡፡ ለዚህ ነው ከእኛ እኩል ሰርፕራይዝ የሆኑት፤

ሴይጣን ቤት ይፈረሳል የሚለው ወሬ የረበሸን በደብዳቤ የተደገፈ ስለኾነ ጭምር ነበር፡፡ ደግሞስ እስከአሁን በዚህ መልኩ ከተያዘ እንዲህ ሆኖ የያዘ ቢያፈርሰው ምን ይፈራል የሚለውም ጥያቄ ነው? በዙሪያዎት ያሉ ሰዎች ቀድመው ሊፈርስ ነው ብለው ይናገሩና መልሰው አይፈርስም የሚለውን አብሳሪ ነን ባይ ሆነዋል፡፡

እርስዎ ቅርስ አፍራሽ ዙሪያዎት ያለው ኮልኮሌ ቅርስ አዳኝ የመሰላችሁበትን ምስጢር ዙሪያዎትን በመፈተሽ ይድረሱበት፤ እውነት እንነጋገርና የከተማውን ሲኒማ ቤት ውስጠ ይዘት እና ለሲኒማ የተፈቀደ ቤት ለሌላ ዓላማ መዋል መጀመሪያ ማንን የሚያስወቅስ ሆኖ ነው? የከተማዎትን ሹማምንት የሚያስነውር ተግባር እኮ ነው?

ቀድሞውኑስ የከተማዋ ቅርሶች ተክለ ቁመና ምን ደረጃ እንደሆነ ሪፖርት ደርሶዎት ያውቃል? እንዲህ አድርገን ብናለማው ተብለውስ ያውቃሉ? የከተማዋ ቅርሶች ሊፈርሱ ነው ሲባል የሚጮህ ተቆርቋሪ የፈጠርነው ቅርሶቹ ቀድሞውኑም ያሉበትን ተክለ ቁመና ለይቶ የሚያስረዳ፤ ተልሞ የሚጓዝ መዋቅር ስለሌለዎት ነው፡፡

የሴጣን ቤት ለሌላ ዓላማ መዋል ብንሰማውም ባንሰማውም አይገርመንም፡፡ ይህ ቅርስ እየተገላበጠ የፓርቲ የንግድ ተቋም ሲሆን መብት ስለሌለን ዝም ያልን ነን፡፡ እንዲህ ሆኖ ቢኖር ከሚፈርስ ስለምንመርጥ አንድ ቀን እንደ ዳግማዊ ምኒልክ ቅጥር ቀን ይወጣለት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

መጋዘን ሆነ የተባለው ቅርስ የተከዘነበት የፓርቲው የንግድ ንብረት በመሆኑ አሁንም ጥፋቱ የመዋቅርዎት እንጂ ሴጣን ቤት አይፍረስ የሚለው ቅርስ ተቆርቋሪ አይደለም፡፡ ጥይት ቢከማችበትም አይገርመንም፤ ይልቁንስ ደስ የሚለው ፈጣን ውሳኔዎን ተስፋ አደርጋለሁ ሸጋ የሲኒማችን ሙዚየም ያድርጉት፡፡ ዙሪያ ገባው ለምቶ እንዲህ ባለው ፋይዳ ያለው ሀሳብ ቢታጀብ ሀገር ያኮራልና፤

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top