Connect with us

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በትራንስፖርትና የሥራ ሰዓት ለውጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሆነ

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በትራንስፖርትና የሥራ ሰዓት ለውጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሆነ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በትራንስፖርትና የሥራ ሰዓት ለውጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሆነ

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በትራንስፖርትና የሥራ ሰዓት ለውጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሆነ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በትራንስፖርት አጠቃቀምና በመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰአት ላይ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

የፌዴራል የትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርአቶ አብዲሳ ያደታ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ በመመሪያዉ መሰረት የግል ወይም የቤት ተሸከርካሪዎችን መጠቀም የሚቻለዉ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑት ዛሬ ሚያዚያ 9 ቀን 2012 ዓ ም ሲሆን፤ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ጎዶሎ የሆኑት ደግሞ ነገ ቅዳሜ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም የፌዴራል ሠራተኞች ሥራ መግቢያ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡30 ሲሆን ከስራ መውጫ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 9፡30 ይሆናል፤ ይህ የሥራ ሰዓት ሽግሽግ ሠራተኞቹ በስራ ሰዓት መካከል የሚያገኙትን የእረፍት ጊዜ አያሳጣቸውም ተብሏል።

አዉቶቢሶች፣ ታክሲዎች፣ የግል ተሸከርካሪዎች፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች እንዲሁም የአዲስ አበባም ሆነ የኢትዮ-ጅቡቲ የመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት በህግ ከተፈቀደላቸዉ የሠው ብዛት 50% ብቻ እንደሚጭኑ ያስገድዳል።

ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች መጫን የሚችለት ከአሽከርካሪው በተጨማሪ አንድ ሠው ብቻ መሆኑን፤ባለሁለት እግር የሞተር ወይም ሞተር አልባ ሳይክሎች ከአሽከርካሪው ሌላ ምንም ሰው መጫን እንደማይፈቀድላቸዉ ተብራርቷል፡፡

የጭነት ተሸከርካሪዎች መጫን የሚፈቀድላቸው ከአሽከርካሪው በተጨማሪ አንድ ሠው ብቻ ነው፡፡

ማንኛውም ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግልት መስጠት የሚችለዉ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት ባለዉ ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፤

ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች በዚህ መመሪያ መሰረት አገልግሎት ሲሰጡ የሚያስከፍሉትን የታሪፍ ጭማሪ በተመለከተ ከመደበኛ ዋጋው 50 ከመቶ ጭማሪ የሚኖረዉ ሆኖ ዝርዝሩ በባለስልጣኑ ይወሰናል፤

በየትኛውም ቦታ የሚገኙ መናሐሪያዎች ማስተናገድ የሚችለት የየዕለት ስምሪት ከመደበኛው ጊዜ የስምሪት መጠን 50% ብቻ ነው

ለክልል መስተዳደር ሠራተኞች ክልሎች ከየራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ አሰራር እንዱዘረጉ ይደረጋል፡፡(ኢኘድ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top