Connect with us

የፖሊስ ማስጠንቀቂያ!!

የፖሊስ ማስጠንቀቂያ!!
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

የፖሊስ ማስጠንቀቂያ!!

#የፖሊስ_ማስጠንቀቂያ!!

በትራንስፖርትና በገበያ ስፍራዎች የሚስተዋለው ቸልተኝነት ሊታረም እንደሚገባ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህብረተሰቡ በመንግስት በኩል የሚወጡ መመሪያዎችን በአግባቡ እንዲተገብር አሳስቧል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያውን በማይተገብሩ ግለሰቦችና አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በዚሁ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በህግ ማስከበር ሂደቱ የፀጥታ አካላት ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር ጀነራሉ ህግን በሚተላለፉ ግለሰቦችና አካላት ላይ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድ አረጋግጠዋል።

በአንዳንድ በትራንስፖርትና በገበያ ስፍራዎች የሚስተዋለው ቸልተኝነት ሊታረም እንደሚገባም አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ እና ለህግ አስከባሪዎች ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

የፖሊስ አባላትም ራሳቸውን ከቫይረሱ በመጠበቅ የተሰጣቸውን አገራዊ ሃላፊነት በቁርጠኝነትና በታማኝነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top