Connect with us

በትግራይ ክልል ለትንሳኤ በዓል የእርድ እንስሳትን ያለፍቃድ ማንቀሳቀስና ማገበያየት ተከለከለ

በትግራይ ክልል ለትንሳኤ በዓል የእርድ እንስሳትን ያለፍቃድ ማንቀሳቀስና ማገበያየት ተከለከለ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

በትግራይ ክልል ለትንሳኤ በዓል የእርድ እንስሳትን ያለፍቃድ ማንቀሳቀስና ማገበያየት ተከለከለ

በትግራይ ክልል ለትንሳኤ በዓል የእርድ እንስሳትን ያለፍቃድ ማንቀሳቀስና ማገበያየት ተከለከለ

በትግራይ ክልል የትንሳኤን በዓልን ምክንያት በማድረግ የእርድ እንስሳትን ያለፍቃድ ማንቀሳቀስና ማገበያየት እንደማይቻል የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ገለጸ።

በኮማንድ ፖስቱ የኢኮኖሚ ግብረ ኃይል አስተባባሪ ዶክተር መብራህቱ መለስ በሰጡት መግለጫ በበዓሉ ምክንያት የሚካሄድ የእንስሳት ግብይት ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት በማያጋልጥ መልኩ እንዲከናወን መመሪያ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

የእርድ እንስሳት ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሰው ከኮማንድ ፖስት ፈቃድ በሚሰጣቸው አካላት ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል።

አንድ አቅራቢ 100 እና ከዚህ በላይ በጎችና ፍየሎችን ለገበያ እንዲያቀርብ መመሪያው የሚያስገድድ መሆኑን የገለጹት የግብረ ኃይሉ አስተባባሪ “ዶሮዎች ደግሞ ከ50 በላይ እንዲሆኑ ተወስኗል” ብለዋል።

ዓላማውም የአቅራቢው ሰው ቁጥር ቀንሶ የእርድ እንስሳትን በማብዛት በሽታውን ለመከላከል መሆኑን አስረድተዋል።

ፍቃድ የሚሰጠውም አቅራቢው ለገበያ ያመጣቸውን የእርድ እንስሳት ብዛት በመቁጠር በመመሪያ መሰረት መሆኑ ሲረጋጋጥ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከዚህ ውጭ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ግለሰብ ንብረቱ እንደሚወረስ አስታውቀዋል።

በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተሞች አረንጓዴ ልማት ዳይሬክተር አቶ አዳነ ገብረፃዲቅ በበኩላቸው ለበዓሉ በአንድ የገበያ ማዕከል መሰባሰብ ቀርቶ በየአከባቢው ግብይት እንዲካሄድ መወሰኑን ተናግረዋል።

ግብይቱም ከሚያዝያ 6/2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ዋዜማ ሚያዚያ 10/2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ከሰዓት በፊት ብቻ እንደሚሆን ተመልክቷል።

(ምንጭ:-ኢዜአ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top