Connect with us

ብ/ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ የተሽከርካሪ ስጦታ ተበረከተላቸው

ብ/ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ የተሽከርካሪ ስጦታ ተበረከተላቸው
Photo Facebook

ባህልና ታሪክ

ብ/ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ የተሽከርካሪ ስጦታ ተበረከተላቸው

የቀድሞ መንግሥት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን የነበሩት ብ/ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ የቤት አውቶሞቢል ስጦታ እንደተበረከተላቸው ተሰማ።

ከ500 ሺ ብር በላይ ግምት ያለውን የማርቼዲስ መኪና ስጦታውን ያበረከቱት ባለሀብቱ አቶ እያሱ ወሰን ናቸው።
ብ/ጀ ካሣዬ ጨመዳ የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊትን ከመስመራዊ መኮንን ጀምረው እስከ ጀነራል መኮንንነት ድረስ ለረጅም ዘመናት ሀገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል ።

ስጦታውን ያበረከቱት አቶ እያሱ ወሰን በንግድ ስራ ፣ሆቴልና አስጎብኚ ፣ በእርሻ ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ አውቶሞቲቭ ዘርፎች… መዋእለ ነዋያቸውን በማፍሰስ እየሰሩ የሚገኙ ስመጥር ባለሀብት መሆናቸው ይታወቃል ።

ባለሀብቱ የተረሱትን የአገር ባለውለታ በማስታወሳቸው ከፍተኛ ምስጋና ተችሯቸዋል።
(#Dechasa Angecha ገፅ ተገኝቶ የተጠናቀረ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top