Connect with us

ዶ/ር ደብረፅዮን እንዴት አሁን ሞት ሞት ሊሸታቸው ቻለ?!

ዶ/ር ደብረፅዮን እንዴት አሁን ሞት ሞት ሊሸታቸው ቻለ?!
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ዶ/ር ደብረፅዮን እንዴት አሁን ሞት ሞት ሊሸታቸው ቻለ?!

ዶ/ር ደብረፅዮን እንዴት አሁን ሞት ሞት ሊሸታቸው ቻለ?!

(ነብዩ ስሑል ሚካኤል ~ የብልፅግና ፓርቲ ትግራይ ቅርንጫፍ ኃላፊ)

ዶ/ር ደብረፅዮን ትላንት ስለኮሮና ቫይረስ አደጋና በእልህና በፍርሃት ለ3 ወር አራዘምነው ስላሉት ህገወጥ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንዲሁም ስለፖለቲካ ብዙ የተናገሩበትና ተስፋ መቁረጣቸው የገለፁበት መግለጫቸው በድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ተከታተልኩት።

በትግርኛ ቋንቋ የተሰጠው መግለጫቸው እንደ ተለመደው ባረጀ የፖለቲካ ቀረርቶና የስም ማጥፋት ዘመቻ የተሞላ ሆኖ ነገርየው ግን ከዛ ከተለመደው ለየት የሚያደርገው አንድ አዲስ ነገር አልታጣበትም፤

ይህም ዶ/ር ደብረፅዮን ስለኮሮና ቫይረስ አደጋ ሲያወሩ “ሞተንም ቢሆን የትግራይ ህዝብ ከዚህ አደጋ ማዳን አለብን፤ ሞተንም ቢሆን ስል እኔንም ጨምሮ ማለት ነው” ያሉበት አስገራሚ ንግግራቸው ነው።

ንግግሩ ያው የተለመደው ካለኛ መሪነትም መስዋእትነትም የትግራይ ህዝብ አይድንም/አይኖርም የሚል ያረጀ ያፈጀ የከኔ ወድያ መሪና ድርጅት ባይ እብሪታዊ ንግግር ቢሆንም ነገርየው ዶ/ር ደብረፅዮን ሞት ማሽተት መጀመራቸው ይህንንም እራሳቸው በአደባባይ መግለፃቸው በብዙ ሰዎች ዘንዳ ግርምትም ትካዜም ፈጥሯል።

የዚህ የመሞት ስሜት (Thanatos/the death instinct) በግልፅ እስከ መግለፅ የደረሰ የጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ምንጮች ሁለት ሲሆኑ አንዱና ዋነኛው ህወሓት ከዚህ ባሃላ (በተለይ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ባሃላ) ፍፁም ያበቃለት ሃይል መሆኑ በመረዳቸውና አምነው በመቀበላቸው የተፈጠረ ነው።

ከዚህ ከህወሓት የፖለቲካ ህይወት የማብቃት የመጨረሻ ማረጋገጫ ምልክት በተጨማሪም ዶ/ር ደብረፅዮን መግለጫው ላይ አፍንጫቸው የመታፈን ስሜት ሲሰማቸውና ለመተንፈስ ሲቸገሩ መታየታቸው በበሽታው ተይዘው ሊሆኑ እንደሚችሉ ትልቅ ጥርጣሬ ፈጥሯል።

“የትግራይ ህዝብ ለማዳን እኔም መሞት ካለብኝ እሞታለሁ” ያሉት ቃልም በአንድ ግዜ ለሁለት ዓይነት ሞት (ለቫይረሱና ለፖለቲካው) መጋለጣቸው ይህም በግልፅ ኑዛዜ እስከ መገለጥ የደረሰ ትልቅ ፍርሃት እንዳለባቸው አሳይቷል።

በመሰረቱ ዶ/ር ደብረፅዮን ከፓርቲያቸው ጋር የማይቀርላቸው የፖለቲካ ሞት እንዲሞቱ እንጂ እንደ ግለሰብ በበሽታ ሆነ በሌላ አደጋ እንዲጎዱ የሚሻ ሰው ይኖራል ተብሎ አይገመትምም፤ አይገባምም!!

የፖለቲካ ሞቱ ግን የግዜ ጣጣውን የጨረሰና እኛም ከህዝባችን ጋር ሆነን በተግባር የታገልለት ስለሆነ ለኛና ለህዝባችን አዲስ የለውጥ ምዕራፍ የሚከፈትበት እፁብ-ድንቅ ኩነት በመሆኑ ከፍተኛ የደስተኝነት ስሜት መፍጠሩ አይቀርም።

ሆኖም ግን በመግለጫው ይህ እፁብ-ድንቅ ኩነት ተመልሶ በእኔ ከሞትኩ ሶርዶ አይብቀል አይነት ከንቱ ልፈፋ ለማጠልሸትና ለመርገም መሞከር በሞት አፋፍ ላይ ደርሻለው ብሎ ሆዳችን ከሚበላ ሰውም ድርጅትም የሚጠበቅ አይደለም።

ከንቱ ልፈፋው “እነዚህ እኔ ነኝ መሪህ የሚሉ ሁለተኛ ደርግ ናቸው፤ ነብሳቸውና የትግራይ ህዝብን የሸጡ ባንዳዎች ናቸው፤ ተጋሩም አይደሉም” የሚሉ ሃላቀር ልፈፋዎች ሰብአዊ ሃዘኔታችንና ኢትዮጵያዊ ቅንነታችን የሚያደበዝዙ ንግግሮች በመሆናቸው መታረም አለባቸው።

በተለይ ትግራዋይነትን እንደ የረጋ የቀበሌ ዘይት በካድሬዎች ለማደልና ለመቀማት ሞሞከሩ ትግራይ ውስጥ በእውነትም የአንድ ሰፈር ካድሬዎች የዘረጉት አፓርታይዳዊ ስርዓት መኖሩ ለአንድ ሺ አንድ ግዜ ማረጋገጫ ይሆናል።

ለማንኛውም ይህ የትግራይ ህዝብ እውነተኛ ትግል ጠልፎ ከዚህ መጣ የማይባል (alien) ስርዓት የዘረጋውና የሞት የመጨረሻ አፋፍ ላይ የደረሰው ህወሓት በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ቀድሞና የዘረኝነት ዲሪቶዉን ጠቅልሎ ይጠፋል።

ይህ ክስተትም ለትግራይ ህዝብና ለመላ የአገራችን ህዝቦች የሙሉ ነፃነት ብስራት ይሆናል።

አዲሱ ትውልድም የማይቀረው ትውልዳዊ መሪነቱ ጨብጦ የትግራይ ህዝብ እንዲሁም መላ የአገራችን ህዝቦች #በብልፅግና ጎዳና ያስጉዛል።

በቃ የፈለገው ይባል ይሄው ነው ከፊት-ለፊታችን ወደኛ እየገሰገሰ ያለው ደማቅ እውነታ!!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top