Connect with us

በሰንበቱ ስለሰንበቴ

በሰንበቱ ስለሰንበቴ
ጎጃም ደብረ ማርቆስ እነ ቆምጫባው የሚመሩት ሰንበቴ ዝክር ላይ

ባህልና ታሪክ

በሰንበቱ ስለሰንበቴ

በሰንበቱ ስለሰንበቴ |  ጎጃም ደብረ ማርቆስ እነ ቆምጫባው የሚመሩት ሰንበቴ ዝክር ላይ እኔ ተገኝቼ አውቃለሁ።
ደምስ አያሌው /ደብረማርቆስ/

በጎጃም ህዝበ ክርስቲያን እሁድ የሰንበት እለት ከቤተክርስቲያን ወይም ከደብር ማንም አይቀርም። ቅዳሴውን አስቀድሶ እንደጨረሰ ካህኑ በሰላም ወደየቤታችሁ ሂዱ ሲሉ የጎጃም ህዝበ -ክርስቲያን በየሰፈሩ፤ በየእድሩ የተቧደኑት የሰንበቴያቸውን ድግስ ሊታደሙ በቤተክርስቲያን ግጥር ግቢ ውስጥ የተሰሩ ትልልቅ እልፍኝ አዳራሾች ውስጥ ተሰባስበው ይቀመጣሉ።

ማዕድ ከመቅረቡ በፊት የተጣላ ሰው ካለ በእድሜ እና በእውቀት የበሰሉ ሰዎች ግራ ቀኙን በማየት አንተም ተው አንተም ተው አባብለው ይቅር ለእግዚአብሔር እንዲባባሉ አድርገው ያስታርቃሉ፤ የታመም ሰው ካለ አምላክ ምህረት እንዲያወርድለት ይማፀናሉ።

የሰንበቴው አባላትም እግሩ ባቀና ጊዜና እና አስቦ በመሄድ የታመመውን እንዲጠይቅ የማህበሩ ሙሴ ወይም ሰብሳቢ መልዕክት ያስተላልፋሉ። በዚህ ሰንበቴ ዝክር ላይ የተቸገረን እንዲረዳዳ የሀዘንና የደስታ ጊዜ ሲኖሩ ጥሪ ይተላለፍበታል።

የሰንበቴ ዝክር በየተራ የሚወጣ ወይም የሚዘከር ሲሆን “ማነው ባለወር ባለሳምንት የመድሐኒያለም ወዳጅ” በማስባል ደጋሹ ለቀጣይ ተረኛ ዋንጫና ሞሰቡን ያስረክባል። ዘካሪው በግራ በኩል ተረኛው ቀጣይ ደጋሽ በቀኝ በኩል ቁመው ስነ_ስርዓቱን ያከናውናሉ።

በዚህ ዝክር የቤት እመቤቶች የጠላ አጠማመቃቸው እየተወደሰ በዋንጫ ዘመራ የሆነውን ጠላ የሰንበቴው አባላት እያጣጣሙ ይጠጣሉ። ተበልቶና ተጠጥቶ ሲያበቃ ተመራርቆ በካህናት ተመርቆ በፀሎት ይጠናቀቃል።

የሰንበቴ ትርጉም – እሑድ እሑድ በቤተ ክርስቲያን የሚሰበሰቡት ክርስቲያን የማኅበር አንድነትን ክርስቲያንነትን ለማስታወቅ የሚጠራቀመው መዋጮ የሰንበት እንጀራና ጠላ ወይንም ገንዘብ ሰንበቴ ይባላል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top