Connect with us

የክልል ወይስ የመላ ኢትዮጵያ አዋጅ ተፈፃሚ ይሁን

የክልል ወይስ የመላ ኢትዮጵያ አዋጅ ተፈፃሚ ይሁን
Photo: Social media

ፓለቲካ

የክልል ወይስ የመላ ኢትዮጵያ አዋጅ ተፈፃሚ ይሁን

የክልል ወይስ የመላ ኢትዮጵያ አዋጅ ተፈፃሚ ይሁን

ሁሉም ዜጋ በቀላሉ እንደሚረዳው እስካሁን ትግራይ እያስተዳደረ የሚገኘው ሃይል በክልል ደረጃ ቀድሞ ያወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የፖለቲካ ይዘትና ዓላማ ያለው አዋጅ እንጂ ከኮሮና ቫይረስ መከላከልና የትግራይ ህዝብ ማዳን ጋር የተያያዘ አይደለም።

አዋጁ ከፖለቲካዊ ዓላማነቱ በተጨማሪ የትግራይ ህዝብን ለማፈንና ለማጉላላት እንዲውል ታስቦ የታወጀ፣ ይህ ዓላማም በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ማለትም በአሰቃቂ ግድያ፣ በኢ-ፍትሃዊ እስርና በመጠን ያለፈ ወከባ እየተገለፀ መቆየቱ ሁላችንም ስንታዘበው ቆይተናል።

በተለይ የክልሉ መዲና በሆነችው መቐለ ላይ እየተፈፀሙ ያሉት የሰብአዊ መብት መጓደሎችና ጥሰቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው በግልፅ እየታየ ይገኛል፤

ለምሳሌ መቐለ ውስጥ 5/7 ሆናቹ ተገኛቹ በሚል 40 ሆነው ወደ ሚታሰሩበት “ግዜያዊ የትምህርት ቤት እስር ቤት” ተወስደው የታጎሩ ወጣቶች መኖራቸው በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኖ ይገኛል፤ እንዲሁም Velocity በመባል የሚታወቀው የፓርቲ ባለስልጣናት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ በሴት እህቶቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘመናዊ ባርነት ተግባርና ለኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ተጋላጭነት ስጋትም ሌላኛው ተጠቃሽ አብነት ነው።

ባጠቃላይ በትግራይ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለፖለቲካ፣ ለአፈናና ለባርነት ማስፈፀምያነት ታስቦ የታወጀ መሆኑ ግልፅ ነው።

በዚህ አጠቃላይ እውነታ ውስጥ አለማቀፋዊ ጥንካሬን እጅጉን እየተፈታተነ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በክልል ደረጃ ብቻ አስቸኳይ አዋጅ ማወጅ ወረርሽኙ ለመከላከል ውጤት አልባ ተግባር መሆኑ ለመገንዘብ አያዳግትም።

ጉዳዩ በህግ አግባብም ጭምር ሲተነተን በክልል ደረጃ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጅ የሚያስፈልገውና የሚፈቀ’ደው በክልሉ አቅም የሚፈታ ችግር ካጋጠመ ብቻ ነው፤ ይህ ማለት የክልል አቅም በቂ ሆኖ ተገኝቶ ከክልሉ ውጭ ያለው አቅምና እርዳታ ደግሞ ‘አያስፈልግም’ በሚል የህግ አንድምታ ስለሚኖሮው ክልሉ የፌዴራልና የአለም አቀፍ አቅም መጠቀም እንዳይችል ሆኖ ወስኗል ማለት ነው።

ነገር ግን አሁን የገጠመን ወረረሽኝ አገራዊ ብቻ ሳይሆን ጭራሽኑ አለም አቀፋዊ ነው። ስለዚህ በክልል ደረጃ የታወጀው አዋጅ የትግራይ ህዝብን ከቫይረሱ ለመከላከል አንዳች አቅም የሌለው አዋጅ በመሆኑ ባስቸኳይ በአገር አቀፋዊ አዋጁ መተካት ይኖርበታል። (እዚህ ላይ በክልሎች ሊኖር የሚችለው አንፃራዊ ሁኔታ ታሳቢ ተደርጎ የተለዩ ደንቦች፣ ውሳኔዎችና እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ዋናው ማዕቀፍ በአገር ደረጃ የሚኖሮው ውሳኔና አመራር መሆኑ መዘንጋት የለበትም)

በዚህ መሰረት በትግራይ ክልል ታውጆ የቆየው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለሌላ ዓላማ እየዋለ ስለሚገኝና ለትግራይ ህዝብ ደህንነት ዋስትና ሊሆን ስለማይችል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወሰነውና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው አገራዊ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በትግራይ ክልልም ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል።

ይህ ባስቸካይ ተፈፃሚ ባለመደረጉ በትግራይ ህዝብ የሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂው የክልሉ “የተለምዶ-መንግስት” መሆኑም ግልፅ መሆን አለበት።

የፌዴራል መንግስትም በተሻለ አገራዊ አቅምና አንድነት አገርና ህዝብ የማዳን ሃላፊነቱ #በምልአት እንዲወጣ እየጠየቅን ቫይረሱን ለመከላከል የባለሞያ ምክሮችና ከሚኒስትሮች ምክር ቤት እየወጡ ያሉት መረጃዎችና ህጎች በመተግበርና እንዲተገበሩ #በመተባበር አለም አቀፋዊ ወረርሽኙ እንድንከላከል አደራ እንላለን።

ነብዩ ስሑል ሚካኤል
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top