Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
Photo: Social media

ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር የኮቪድ-19 ስርጭት በሚገታበት ሁኔታ ዙሪያ የስልክ ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት እና የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ስለሚያከናውኑት ተግባር የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተሩን አመስግነዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ይህ አስጨናቂ ጊዜ ከምንጊዜውም በላይ የጋራ አመራርን እንደሚጠይቅ አረጋግጠውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይም አመራራቸው ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን መሆኑን በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ይጠቁማል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top