በአለም ላይ በአገራት ደረጃ የኮቪዲ-19 ምርመራ ምን ይመስላል?
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ የሰው ልጅ ስጋት መሆኑ ከታወቀ ወዲህ አገራት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን እና ዜጎቻቸውን በለይቶ ማቆያ በማስገባት እየመረመሩ ይገኛል፡፡
ኮሮና በቻይናዋ ዉሃን ከተማ በታህሳስ 2019 መከሰቱ ከተነገረ ወዲህ በፍጥነት ተዛምቶ ከ1.61 ሚሊዮን ሰዎችን አጥቅቷል፡፡
በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች መቶ ሺ ያለፉ ሲሆን ከበሽታው ያገገሙት ደግሞ ከ370ሺ በላይ ናቸው፡፡
የተያዙ፣ ያገገሙና የሞቱት ሰዎች ይፋ የሚደረጉበት መንገድ ደግሞ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ገብተው በሚያሳዩት የምርመራ ውጤት ነው፡፡
ታዲያ አገራት ለዜጎቻቸው በአሁኑ ወቅት ምን ያህል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያደረጉ ይገኛል? አናዶሉ ወርልድ ሜተርስ አጠናው ብሎ ያቀረበውን ሪፖርት እንመለከታለን፡፡
በአውሮፓ እስካሁን ጀርመን ከ1ሚሊዮን 317 ሺ በላይ ምርመራ ስታደርግ፣ ፈረንሳይ ከ333ሺ 800 መቶ በላይ በመመርመር ትከተላለች፣ ታሏቋ ብሪታንያ ደግሞ 298ሺ 169 ገደማ ምርመራዎችን አድርጋለች፡፡
ይህም ጀርመን ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መኃል 15ሺ ሰባት መቶ በላዩን ምርመራ እንደምተደርግ ሲያሳይ፣ ፈረንሳይ ከ5ሺ 1መቶ በላይ ሰዎችን ስትመረምር ፣ ታሏቋ ብሪታንያ ደግሞ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ከ4ሺ ሶስት መቶ በላይ ሰዎችን ትመረምራለች ማለት ነው፡፡
ጣልያን በበኩሏ 853ሺ 400 ገደማ ለሚሆኑ ሰዎች ምርመራ ያደረገች ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ለ14 ሺ 114ቶቹ ምርመራ እያደረገች ነው ተብሏል፡፡
ከፍተኛ የኮሮና ተጠቂ ከተመዘገበባቸው አገራት መካከል በሆነችው ስፔን ደግሞ እስከ አሁን ከ355 ሺ በላይ ምርመራዎች ሲደረጉ ይህም ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መካከል ከ7ሺ አምስት መቶ በላዩ ምርመራ እንደሚያደርጉ ነው የታወቀው፡፡
በኤዥያ በትክክል ምን ያህል ምርመራዎች እንደተደረጉ እንደ ሆነ አይታወቅም ያለው ሪፖርቱ ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ህንድ 117 ሺ 584 ገደማ ምርመራዎችን አድርጋለች፡፡
273 ሚሊዮን ሰዎች በሚኖሩባት ኢንዶኖዢያ 17ሺ ስድስት መቶ ምርመራዎች ሲደረጉ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መካከል ለ65 ቱ ብቻ ምርመራ እንደምታደረግ ነው የተጠቀሰው፡፡
ፓኪስታን 54ሺ 7 መቶ ገደማ ምርመራ ስታደርግ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መካካል ለ248ቱ ምርመራ እያደረገች ነው፡፡
ጃፓን ደግሞ እስከ አሁን ከ64ሺ 380 በላይ ምርመራዎችን ያደረገች ሲሆን ከአንድ ሚሊየን ዜጎች ውስጥ 509 ሰዎች ይመረመራሉ ተብሏል፡፡
ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ከ503ሺ በላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራዎችን ያደረገች ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ከ9ሺ 800 በላይ ለሚሆኑት ምርመራ እያደረገች መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም አገሪቷ በሽታውን ለመከላከል ፈጣን የሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ ቀዳሚዋ መሆኗ ነው የተነገረው፡፡
ሩሲያ እስከ አሁን ከ1 ሚሊዮን 90 ሺ በላይ ነዋሪዎቿን መርምራለች፣ ይህም ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ 7ሺ 470 ገደማ ለሚሆኑት ምርመራ ታደርጋለች ማለት ነው፡፡
በቻይና ግን እስከ አሁን በአገሪቱ መንግስት ገልጽ የሆነ መረጃ አለመሰጠቱን ሪፖርቱ አሳይቷል፡፡
ኢራን ከ231ሺ 3መቶ በላይ ሰዎችን የመረመረች ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መካከል 2ሺ ሰባት መቶ ገደማውን ትመረምራለች ነው የተባለው፡፡
ከ115 ሺ 580 በላይ የኮሮና ምርመራዎችን ያረገችው ሳዑዲ አረቢያ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መካከል 3ሺ 320 ለሚሆኑት ብቻ ምርመራ እያደረገች መሆኑ ተገልጿል፡፡
ግብጽ እስከ አሁን ድረስ 25ሺ ምርመራ ስታደርግ ከ1 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ደግሞ ለ244 ሰዎቹ ምርመራ ታደርጋለች፡፡
ከ117 ሺ 3መቶ በላይ ምርመራ ያደረገችው እስራኤል በሚሊዮን 13ሺ 557 ገደማ ምርመራዎችን እንደምታደርግ ነው ተጠቁሟል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ በህዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆነቸው ናይረጄሪያ ከ206 ሚሊዮን ዜጎቿ መካከል ለ5ሺ ሰዎች ብቻ ምርመራ ስታደርግ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች መካከል ለ24 ሰዎች ነው ምርመራ እያደረገች የምትገኘው፡፡
እስከ አሁን 65 ኬዞች የተመዘገቡባት ኢትዮጵያ 3ሺ 232 %