Connect with us

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላዎች ነገ ይፋ ያደርጋል

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላዎች ነገ ይፋ ያደርጋል
GettyImages

ህግና ስርዓት

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላዎች ነገ ይፋ ያደርጋል

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላዎች ነገ ይፋ ያደርጋል

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የፀደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የተጣሉ ክልከላዎችን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

በአዋጁ አንቀጽ 4 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 መሰረት የሚጣሉ የመብት እገዳዎች፣ እርምጃዎች እንዲሁም ግዴታዎችን በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቅዳሜ ሚያዚያ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፃል።

ህብረተሰባችን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ያልተረጋገጡ ወሬዎችን እና መረጃዎችን ከመሰማት እንዲቆጠብ አሳስቦ፣ በአዋጁ መሰረት ከሚዉጡ ህጎች ጋር በተያያዘ ማብራሪያ የመሰጠት ኃላፊነት በተሰጠዉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል እስከሚሰጥ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቅ ጠይቋል።

ሌሎች ምንጮች እንደጠቆሙት የሚኒስትሮች ምክርቤት በነገው እለት በሚያደርገው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ደንብ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top