Connect with us

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለዶ/ር ቴድሮስና አድሀኖም ድጋፋቸውን ሰጡ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለዶ/ር ቴድሮስና አድሀኖም ድጋፋቸውን ሰጡ
Photo: Social media

ፓለቲካ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለዶ/ር ቴድሮስና አድሀኖም ድጋፋቸውን ሰጡ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ተገቢውን ስራ አልሰራም በሚል በአሜሪካ መንግስት እና በሌሎች አካላት በድርጅቱ እና በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ላይ ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።

ይህንን ተከትሎም የአፍሪካ ህብረትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በአሜሪካ መንግስት አና በሌሎች አካላት የሚፈጠሩ ጫናዎችን በመቃወም ድጋፋቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት እና ለድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትዊተር ገፃቸው እንደገለፁት፥ አሁን ላይ በዓለም ላይ ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባው የሰዎችን ህይወት ማዳን ነው ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በዶክተር ቴድሮስ አመራር ሰጪነት በጣም በሚያስፈልገን ወቅት ላይ የተሰጠውን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ እየተወጣ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ ጊዜ ልንሰጣቸው ይገባልም ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነው ኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የበርካቶችን ለሞት እየዳረገ ነው፤ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን አካላት መጠበቅ እና መደገፍ ይጠበቅብናል ሲሉም ገልፀዋል።

አሁን ያለንበት ጊዜ ጣት የመቀሳሰሪያ ጨዋታ የምንጫወትበት አይደለም ሲሉም ፕሬዚዳንቷ ገልፀዋል።

የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳም፥ ለዓለም ጤና ድርጅት እና ለዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የዓለም ጤና ድርጅት እና የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አመራር የተለየ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍም፥ የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አመራርነት በምንም የማይተመን ነው ሲሉም ገልፀዋል።

የአፍሪካ ህብረትም የዓለም ጤና ድርጅት እና ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን በሙሉ አቅሙ እንደሚደግፍም ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መኸመትም፥ የአሜሪካ መንግስት በዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ዓመራር ላይ የከፈተው ዘመቻ በጣም እንዳስገረማቸው በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ መኸመት፥ የአፍሪካ ህብረት የዓለም ጤና ድርጅት እና ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍም አስታውቀዋል።

አሁን ትኩረት ሊደረግ የሚገባው በጋራ በመሆን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን መዋጋት ላይ ነው፤ የተጠያቂነት ጉዳይ ጊዜውን ጠብቆ ይደርሳል ብለዋል።

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜም፥ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሀሳብ ሙሉ በሙሉ እንደሚስማሙ በትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍሪካውያን ሙሉ ድጋፍ አላቸው ሲሉም ነው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የገለፁት።

የናይጄሪያ መንግስትም ለዓለም ጤና ድርጅት እና ለዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሙሉ ድጋፉን የገለፀ ሲሆን፥ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተገቢ ዝግጅትና ምላሽ እንዲሰጥ የዓለም ጤና ድርጅት ለሰጠው መመሪያ እና አመራርም ምስጋና አቅርቧል።(ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top