Connect with us

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እንቅስቃቄ በገደበችው ሩዋንዳ 5 ወታደሮች በአስገድዶ መድፈር ተከሰሱ

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እንቅስቃቄ በገደበችው ሩዋንዳ 5 ወታደሮች በአስገድዶ መድፈር ተከሰሱ
Photo: Public Radio International

ህግና ስርዓት

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እንቅስቃቄ በገደበችው ሩዋንዳ 5 ወታደሮች በአስገድዶ መድፈር ተከሰሱ

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እንቅስቃቄ በገደበችው ሩዋንዳ 5 ወታደሮች በአስገድዶ መድፈር ተከሰሱ

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል በመላ ሀገሪቱ እንቅስቃሴዎች በተገደቡባት ሩዋንዳ 5 ወታደሮች በአስገድዶ መድፈር ተከሰዋል፡፡

የአስገድዶ መድፈር ወንጀሉ የተፈፀመው በዋና ከተማ ኪጋሊ ሰዎች በብዛት በሚኖሩበት ንያሩታራማ በተሰኘው መንደር ነው ተብሏል፡፡

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱት አምስት ወታደሮችም መንግስት ያወጣውን መመሪያ በመንደሩ ሲያስተገብሩ የነበሩ ናቸው፡፡

የመንደሯ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሴቶችን ከመድፈር ባለፈ ወታደሮቹ ወንዶችን ሲደበድቡ እና ሲሰርቁ ነበር፡፡

የሩዋንዳ መንግስት የአለም የወቅቱ የራስ ምታት የሆነውን ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ሰዎች ወደ ውጭ እንዳይወጡ ወታደሮች አሰማርታለች፡፡

ባለፈው ሳምንት መንግስት ያወጣውን ቤት የመቀመጥ ግዴታ ተላልፈው ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ እስካሁን 84 ዜጎቿ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

ምንጭ፡ቢቢሲ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top