Connect with us

በወንጀል ከተጠረጠሩ ሰዎች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተያዙ

በወንጀል ከተጠረጠሩ ሰዎች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተያዙ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

በወንጀል ከተጠረጠሩ ሰዎች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተያዙ

በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለያዩ የክፍለ ከተማው አካባቢዎች ላይ በተለዩ የሌባ ተቀባይ ቤቶች ላይ በተሰራ ጥናት የተለያዩ ተጠርጣሪዎችንና የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ከየካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በተደረገው ጥናት 5 መቶ 67 ሞባይሎች 14 ላፕቶፖች ፣14 ታብሌት ሞባይሎች እና የተለያዩ የጀሮ ማዳመጫ ሂር-ፎኖች ተይዘዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ም/ኢ/ር ፀጋዬ አህመድ በሰጡን ማብራሪያ በ19 ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ 20 ተከሳሾች የተያዙ ሲሆን በጉዳዩ ላይ 43 ከሚሆኑ ምስክሮች ቃል መቀበላቸውን ተናግረዋል፡፡

በክፍለ ከተማው ጥናት ከተደረገባቸው አካባቢዎች ውስጥ ካራ ማራ፣ኤድናሞል፣22፣ገርጂ ፣መገናኛና ኤር-ፖርት ዋነኞቹ አካባቢዎች እንደሆኑ የነገሩን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሀላፊ ኢ/ር ያሬድ ታረቀኝ ናቸው፡፡አያይዘውም በተለያዩ ቦታዎች የሚፈፀሙ የመኪና ዕቃ፣የኪስ ስርቆትና የቅሚያ ወንጀሎች መበራከታቸውን መነሻ በማድረግ በተደረገ ጥናት የተገኘ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚያደርጋቸው የተለያዩ ጥረቶች የተዘናጋ የመሰላቸው ሕገ-ወጦች መበራከት ሌላኛው ለወንጀሎቹ መፈፀም ምክንያት መሆኑን በጥናታቸው የደረሱበት መሆኑን ገልፀው፡የወረርሽኙ መስፋፋትን በመከላከል ረገድ ከሚሰሩት የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎች ጉን ለጉን ሰላምና ፀጥታን የማስጠበቅ ተግባራቸውን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ም/ኢ/ር ፀጋዬ አህመድ በበኩላቸው የተለያዩ ላፕቶፖች፣ሞባይሎችና ታብሌቶች በክፍለ ከተማው በኤግዚቢትነት የሚገኙ መሆኑን ጠቁመው ንብረት ጠፋኝ የሚሉ ግለሰቦች በቂ ማስረጃዎችን ይዘው በመቅረብ መውሰድ እንደሚችሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡(አ/አ ፖሊስ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top