Connect with us

ሁለቱ ብርቱዎች፤ ሁለቱ ዶክተሮች፣

ሁለቱ ብርቱዎች፤ ሁለቱ ዶክተሮች፣ ሁለቱ የፈተና ከዋክብት፤ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

ሁለቱ ብርቱዎች፤ ሁለቱ ዶክተሮች፣

ሁለቱ ብርቱዎች፤ ሁለቱ ዶክተሮች፣ ሁለቱ የፈተና ከዋክብት፤ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን – ቴዎድሮስና ሊያ
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ሁለቱም ብርቱዎች ናቸው፡፡ መልካም ስራቸው እሷ ሀገሯን እሱ ዓለምን በጤናው ዘርፍ እንዲመሩ አስመረጣቸው፡፡ ወንበሩ ከምቾች ይልቅ እሾህ ነበር፡፡ እንቅልፍ አልባ ህይወትን ይመሩ ዘንድ አጋጣሚ አስገደዳቸው፡፡

ሰውዬው ብርቱ ቢሆኑም የመጣውን መቅሰፍት እንመክት ብለው አንድነትና ገንዘብን ጠየቁ፡፡ ሊሆን ያለውን ነገር እንቅደመው አሉ፡፡ ዓለም ጥድፊያ ላይ ነበር፡፡ እንዲህ ያለ አፍሪቃዊ አይመክረኝም ባይ ትምክህተኛ ነበር፡፡

ውሎ አድሮ ውጤቱ ከፋ፡፡ ለወረርሽኙ ሩቅ ነን ያሉት ሟች መቁጠር ጀመሩ፡፡ እንዲህም ሆኖ አሁንም ያለ እረፍት የሚባትሉት የዓለም የጤና ድርጅት መሪ ከኒሺያንና ከሜዳይ ይልቅ መጥፎ ስም አተረፉ፡፡ እሳቸው አፍሪቃዊ ናቸውና፤ እሳቸው የኔ የሚላቸው የዓለም ሚዲያ የለምና፤ እሳቸው አንድ ጥቁር ናቸውና፤

እዚህ ደግሞ ሀገራቸው ላይ ቀድሞ እኒህ ሰው ቦታ ዛሬ የተቀመጡት ዶክተር ሊያ በተሾሙ ማግስት ቲተራቸው እጃቸው ሳይገባ ኮሮና አፍሪቃ ገባ፡፡ ከዚያ በኋላ አበሳው በረታ፡፡ ከዚያ በኋላ ኡኡታ ሆነ፡፡ በደሃ ሀገር የዓለም ሀብታም ሀገር ያልቻለውን በሽታና ወረርሺኝ ለመመከት ከመበርታት የሚበልጥ ጀግንነት የለም፡፡

እኒህን ሴት በተመለከተ አሌክስ አብረሃም ጥሩ አድርጎ ጽፎታል፡፡ አንዳንድ ወንበር እንዲህ ነው፡፡ ስልጣን ሳይሆን እሳት ይሆናል፤ ምቾቱ ሳይሆን አበሳው ይገዝፋል፡፡ የምስራች ሳይሆን ሰቀቀን ነጋሪ ያደርጋል፡፡ እንኳን ለቤተሰብ ለራስ የሚተርፍ ግዜን ይነሳል፡፡

ሁለቱም ሹመኞች ጠንካሮች ናቸው፡፡ ዓለምን ካንበረከከ ወረርሺኝ ጋር ተናንቀዋል፡፡ እኛኛውን ዓለም አላደምጥ ብሎ ዛሬም እፎይታን እንደናፈቁ ነው፡፡ እኚህኛዋን ብርቱ ሴት ደግሞ ኢትዮጵያ ጆሮ ነስታቸዋለች፡፡ ስኬታቸው የራሳቸው አልነበረም፡፡

ያሰቡት ሲሳካ ትውልድ ይተርፋል፤ ዘር ይቀጥላል፡፡ ዓለም ትፈወሳለች፡፡ የአንዳንድ ሰው ስኬት የፍጥረት ስኬት የሚሆነው እንዲህ ነው፡፡ ድካማችሁን የሚቆጠር አምላክ ውጤታችሁን እኛን በማትረፍ ለሁላችን መልካሙን ያደረግ ዘንድ ምኞታችን ነው፡፡ ምኞት ብቻ ለድል ስለማያበቃን ወገንን ጠብቆ ራስን ለማትረፍ የራሳችንን ግዴታ እንወጣ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top