Connect with us

ከሕገወጥ የሳኒታይዘር እና አልኮል አምራቾች ይጠንቀቁ!

ከሕገወጥ የሳኒታይዘር እና አልኮል አምራቾች ይጠንቀቁ!
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

ከሕገወጥ የሳኒታይዘር እና አልኮል አምራቾች ይጠንቀቁ!

ከሕገወጥ የሳኒታይዘር እና አልኮል አምራቾች ይጠንቀቁ!
ዝርዝራቸው እነሆ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች (ሳኒታይዘሮች) በህጋዊ መንገድ በስፋት ተመርተው ገበያ ላይ እንዲቀርቡ ጊዚያዊ ፈቃድ በመስጠት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ባደረገው የገበያ ጥናትና ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ሳይመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳያገኙ በህገ-ወጥ መልክ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ አምርተው ለገበያ የሚያቀርቡ የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት መኖራቸውን ባለስልጣን መ/ቤቱ አክሎ ገልጿል፡፡

ያልተመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያላገኙ እንዲሁም ጥራታቸውና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ ያላቸውን ተከታዮቹን የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል፡-

1.!መላመሳኒታይዘር/ Mela Sanitizer
2. ናይሮቢ ሳኒታይዘር/ Narobi Sanitizer
3. ሐበሻ ሳኒታይዘር/ Habesha Sanitizer
4.ፎም ሳኒታይዘር/ FOM Sanitizer
5.ጂ.ኤስ.ቲ ሳኒታይዘር/ GST Sanitizer
6.ሲልቫ ሳኒታይዘር/ Silva Sanitizer
7. የሮ ሳኒታይዘር/Yero Hand Sanitizer
8. አደይ ሳኒታይዘር/Adey Hand Sanitizer
9. አቢሲኒያ ሳኒታይዘር/Abyssinia Hand Sanitizer
10. ታፍ አልኮል/TAFF አልኮል ናቸው።

ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች ገበያ ላይ ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ ወይም ለፖሊስ እንዲያሳውቅ አሊያም ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ የስልክ መስመር 8482 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

(ምንጭ:- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top