Connect with us

በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፎ ያለውን አንድ የውጪ ሃገር ዜጋ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ

በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፎ ያለውን አንድ የውጪ ሃገር ዜጋ በቁጥጥር ስር አዋለ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፎ ያለውን አንድ የውጪ ሃገር ዜጋ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ

የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተሳትፎ ያለውን አንድ የውጪ ሃገር ዜጋን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ግለሰቡ በርካታ የኢትዮጵያን ብር ፣ የአሜሪካ ዶላር እና ዩሮ ይዞ ተገኝቷል፡፡

በኮንስትራክሽን የስራ ዘርፍ የተሰማረው እና የውጪ ሀገር ዜግነት ያለው ግለሰብ 22ሺ 831 የአሜሪካ ዶላር ፣ 2ሺ600 ፓውንድ ፣ 2ሺ 700 ዩሮ እንዲሁም 553ሺ 550 ብር ይዞ የተገኘው መጋቢት 25 ቀን 2012 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ግሎባል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ነው፡፡

የቤሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡ ከዋና ስራው ባሻገር በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፎ እንዳለው ከህብረተሰቡ የደረሳቸውን መረጃ መሰረት በማድረግ ባደረጉት ክትትል እንደተያዘ የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ዘሪሁን ተፈራ ገልፃዋል፡፡

ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያሳርፍ ኢንስፔክተር ዘሪሁን ተናግረው በጥቁር ገበያ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ የሚመነዝሩ የሀገራችንም ሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎች ከህገ-ወጥ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ:- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top