Connect with us

ሙስጠፌንማ በክፉ አትመልከቱት ገና ሀገራችንን ይመራል

ሙስጠፌንማ በክፉ አትመልከቱት ገና ሀገራችንን ይመራል ብለን ለኢትዮጵያ ያጨነው ሙሽራ ነው
Photo: Social media

ፓለቲካ

ሙስጠፌንማ በክፉ አትመልከቱት ገና ሀገራችንን ይመራል

ሙስጠፌንማ በክፉ አትመልከቱት ገና ሀገራችንን ይመራል ብለን ለኢትዮጵያ ያጨነው ሙሽራ ነው፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

በሱማሌ ክልል የሆነ ነገር ተንኮሻኩሾ እንደነበረ ሰማን፤ ዜናው ብዙ ስም ቢሰጠውም ከሁሉም መረዳት የቻልኩት ግን አቶ ሙስጠፌን ለማደናቀፍ የተሞከረ ሙከራ መኖሩን ነው፡፡ አቶ ሙስጠፌ ከለውጡ መሪዎች ስኬታማውና ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ የደፈረሰውን ክፍል በኢትዮጵያ ብቸኛው የሰላም ቀጠና አድርጎታል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሱማሌዎች እንዲህ ሀገር የመምራት እድል ካገኙ በሳል ልጆች ወልደው ማበርከት እንደሚችሉ ያሳመነ መሪ ነው፡፡

በክልሉ የእምነት የብሔርና የፖለቲካ መጠፋፋት እንዳይኖር ተግቶ ሰርቷል፡፡ ጅግጅጋ ሰላማዊ ዩኒቨርሲቲዋ ሀገር ሲታመስ ኮሽ ያላለ ሱማሌዎች ለረዥም ዘመን ያጡትን ሰላም እውን አድርገው እንዲኖሩ ምክንያት የሆነ ልሂቅ ነው፡፡

ሙስጠፌ መንገደኛ አይደለም፡፡ ጭቆናና አፈናን የታገለ ጀግና ነው፡፡ ሙስጠፌ ስልጣን ናፋቂ አይደለም ከዚህ የሚበልጥ ህዝብ የመጨቆን እድል የነበረው እንቢኝ ብሎ አፋኙን የአብዲሌ ሥርዓት የታገለ ቆራጥ ነው፡፡

ሙስጠፌም ሆነ የሚመራው ክልል ህዝብ ሰላምን የሚሹ ሃይማኖተኞች መሆናቸው የታወቀው ስውሩ እጅ ከሱማሌ ምድር ሲሰበሰብ ነበር፤ ከዚያ በኋላ የተመሰገ መሪ፣ የተመሰገ ክልል፣ የተመሰገነ ህዝብ ሲነሳ ሙስጠፌ፣ ሱማሌና ሱማሌዎች ሆኑ፤

ይሄንን ሰው ማደናቀፍ ሀገር ይጎዳል፤ አቶ ሙስጠፌ አጭተነዋልና ሙሽራ ነው፡፡ ገና ኢትዮጵያን ይመራል፡፡ ገና አራት ኪሎ በክብር የምናስቀምጠው እጩ ነው፡፡ ሙስጠፌ ብዙ የምናስበው ለብዙ የምንሳሳለት ጀግና ነው፡፡

ጀግናውን በክፉ አታስቡት፤ ጀግናው የሱማሌ ክልል መሪነቱ የበዛበት ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ይህ ሰው ኢትዮጵያን ለመምራት የሚችል ልበ ብሩህ፣ አቅም ያለው ጀግና ነው፡፡ የሀገርን ጀግና ለሀገር ስትሉ በክብር ጠብቁት፤ የሱማሌ ክልል ህዝብ ኢትዮጵያ ትልቅ አደራ የሰጠችው ይመስለኛል፤ ያም የነገዋን መሪዋን ሙስጠፌን ነው፡፡

Continue Reading
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top