Connect with us

ኢትዮጵያውያን አንድ እድል አለን

ኢትዮጵያውያን አንድ እድል አለን፤
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

ኢትዮጵያውያን አንድ እድል አለን

ኢትዮጵያውያን አንድ እድል አለን፤
ስቅለትን በጋራ ለመስገድ ዛሬ ቤት ተቀምጦ እንደ አባቶች ትዕዛዝ መጸለየ፤ ረመዳንን በጀመዓ ለመስገድ የኡላማዎችን ምክር ሰምቶ ዛሬ በየቤቱ መስገድ፤ አንድ ሳምንት መጨከን ካቃተን ብዙ ሳምንት ዋጋ እንከፍላለን፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ 

አሁን ከምርጫ ጋር ተፋጠናል፡፡ የኢትዮጵያ የእምነት አባቶች ከአለማወቅ ጠብ ውስጥ እንዳንገባ እየቀደሙ መንገድ መርተዋል፡፡ በሚመሩት መንገድ በመመራት ይኼን የጭንቀት ወራት ማለፍ የራሳችን ምርጫ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዲዮሱ ከዚህ በኋላ ምዕመናን በየቤታቸው ሆነው ጸሎት በማድረግ እንዲቆዮ አስታውቋል፡፡ ጥቂት አገልጋዮች ደጆቿ የማይዘጋውን ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሉ መወሰኑን ገልጾዋል፡፡

ከውሳኔውም በኋላ ውሳኔውን አለማክበር ታይቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያናት አካባቢ ዛሬም ብዙ ጭንቅንቅ ይታያል፡፡ እንዲህ ያለው ልማድ በከተሞች ገዝፎ ተስተውሏል፡፡ የሚባለውን መስማት የምንፈልገው ጋር ያደርሰን ነበር፡፡ ለምሳሌ የስቅለትን በዓል አብሮ እንዳለመስገድ ከባድ የለም፡፡ ዛሬ በተናጥል በየቤቱ በጸሎት ቆይቶ ወረርሺኙን ድል ማድረግ ካልተቻለ ስቅለትን ያህል ቀን በተናጥል ለማሳለፍ እንገደዳለን፡፡ ትንሳኤን ያህል በዓል በምን ሁኔታ ልናሳልፍ እንደምንችል መገመት የሚቻለው ከዛሬው ሁኔታ ነው፡፡

በሌላ በኩል ህዝበ ሙስሊሙም ከኡላማዎቹ መልእክት ተላልፎለታል፡፡ መልእክቱ አሁን በጋራ መስገድን አቁሞ ሶላት በተናጥል እንዲሆን ይመክራል፡፡ ይሄንን ተቀብሎ ወረርሽኙን በመረባረብ ድል ማድረግ ካልተቻለ ቀጣዩን ረመዳን በተናጥል ለማሳለፍ ግድ የሚልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

የሳውዲ መንፈሳዊ ጉዞዎች የተሰረዙት በዚሁ በሽታ ስጋት ነው፡፡ በዚሁ በሽታ ስጋት የሰው ልጅ ሌላው ዓለም ሁሉን ነገር ትቶም መዳን አልቻለም፡፡ እኛ ትልቅ እድል አለን፤ አንድ ሳምንት ዋጋ ከከፈልን ድል አድርገን ሁሉም ነገር ትዝታ ይሆናል፡፡

አንድ ሳምንት መስዋዕትነት መክፈል ካቃተን እገዳው ከማንም ሳይመጣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ብዙ ሳምንት ራሱን ያግዳል፡፡ የሚቀለውን መምረጥ ላይ አሁንም ብልጦች መሆን እያቃተን ነው፡፡ በተናጥል በመሰንበት፤ በጋራ አንድ ላይ ለአንድ ዓላማ ቆመን ወደኖርንበት የአንድነት ኑሮ እንመለስ፤

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top