Connect with us

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ
Photo: Social media

ዜና

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በስጦታና በቦንድ ሽያጭ ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን በስጦታና በቦንድ ሽያጭ ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገልፀዋል፡፡

የግድቡ የአፈጻጸም ሂደት 72.4 በመቶ መድረሱን የግድቡ ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ግድቡ የተመሰረተበትን ዘጠነኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት እየጠካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ የግድቡ የሲቪል ስራ ከ86 በመቶ በላይ መድረሱን የተጠቀሰ ሲሆን የኤልክትሮ ሜካኒካል ስራው ደግሞ 44 በመቶ መድሱንም ተገልጿል፡፡

የግድቡን ግንባታ በማፋጠን በዚህ ዓመት ውኃ ለመያዝ እየተሰራ እንደሆነ እና ለዚህም ተገቢውን ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስጋትን ለመቀነስ እንዲያስችል የተለያዩ መከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም እና እርቀትን በመጠበቅ የግድቡ ስራዎች እንደ ቀድሞው ሁሉ ስራቸው እየተከናወነ መሆኑን በውይይቱ ተመላክቷል፡፡

EBC

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top