Connect with us

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በግድቡ ላይ ለመምከር በግብፅና በኢትዩጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስተር በግድቡ ላይ ለመምከር በግብፅና በኢትዩጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
Sudanese Prime Minister Abdallah Hamdouk (Photo: Suna News Agency)

ማህበራዊ

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በግድቡ ላይ ለመምከር በግብፅና በኢትዩጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ በግድቡ ላይ የሚደረገዉን ድርድር ለማስቀጠል ያሰበ ጉብኝት በግብፅና በኢትዮጲያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑን በፅህፈት ቤታቸው በኩል ይፋ ማድረጋቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ በግድቡ ዙሪያ እየተደረገ የነበረዉን ድርድር ለማስቀጠል በማሰብ በግብፅና በኢትዮጲያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑን ያሳወቁት በያዝው ሳምንት መጀመሪያ ነበር፡፡

እንደዘገባዉ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ይህንን ያስታወቁት ከአሜሪካዉ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑቺን ጋር በስልክ ዉይይት በኋላ ነዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልክ የደወሉበት ዋና ጉዳይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት ለደረሰዉ ጉዳት የተሰማቸዉን ሀዘን ለመግለጽ ሲሆን እግረ መንገዳቸዉንም በሁለቱ ሀገራ ሊያደርጉት ስላሰቡት ጉብኝት መነጋገራቸዉን ዘገባዉ አመላክቷል፡፡

አብደላህ ሀምዶክ በቅርቡ ወደ ካይሮና በአዲስ አበባ በማቅናት ሁለቱ ሀገራት በህዳሴዉ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያደርጉት የነበረዉንና ኋላም ያለስምምነት የተቋረጠዉን ድርድር እንዲቀጥሉና የቀሩ መሰረታዊ ግዳዮች ላይ ከስምምነት እንዲደርሱ ግፊት የማድረግ ሀሳብ እንዳላቸዉ ገልፀዋል ፡፡

በአሜሪካ የተካሄደዉ የዉይይት ሂደት ትልቅ ስኬቶች የተመዘገቡበት ስለሆነ ሀገራቱ ድርድሩን መቀጠላቸዉ አግባብ እንደሆነም ገልጸዋል ሲል ዘገባዉ አስነብቧል።

ባሳለፍነው ወር ሱዳን፤ ኢትዮጵያና ግብጽ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ወደ ሚደረገው ድርድር በመመለስ ከስምምነት እንዲደርሱ ጥሪ ማቅረቧ ይታወቃል። ሱዳን የአረብ ሊግ ያቀረበውን ግብጽን የሚደግፍ የውሳኔ ሐሳብ እንደማትቀበለው ካሳወቀች በኋላ ነው ይህንን መግለጫ በማውጣት ለሁለቱ አገራት ጥሪ ያቀረበችው።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top