Connect with us

ከለይቶ ማቆያ የተሰወሩ በፖሊስ እየተፈለጉ ነው

ከለይቶ ማቆያ የተሰወሩ በፖሊስ እየተፈለጉ ነው

ህግና ስርዓት

ከለይቶ ማቆያ የተሰወሩ በፖሊስ እየተፈለጉ ነው

በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የአለም ሀገራትን እያሳሰበ ያለዉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሀገራችን ኢትዮጵያ እንዳይስፋፋ መንግስት በየጊዜዉ የተለያዩ መመሪያዎችን ለማህበረሰቡ በመስጠት በቅድመ መከላከል ዙሪያ በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በቅርቡም ለጋራ ደህንነት ሲባል መንግስት አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ጊዜ በማዉጣት ከዉጭ ሀገር የሚመጣ ማንኛዉም ሰዉ ወደ ማህበረሰቡ ከመቀላቀሉ በፊት ለ 14 ቀናት በተዘጋጀለት ማዕከል መቆየት እንዳለበት መመሪያ ማዉጣቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም አቅም የሌላቸዉ ሰዎች መንግስት ባዘጋላጀላቸዉ የማቆያ ቦታዎች፣ አቅም ያላቸዉ ደግሞ በራሳቸዉ ወጪ በተመረጡ ሆቴሎች እንዲቆዩ እየተደረገ ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ከዉጭ ተመላሾች ለ14 ቀናት በመቆየት በቂ ምርመራ ማድረግ ሲገባቸዉ ከማዕከላቱ የጥበቃ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር አንድ እና ሁለት ቀን ብቻ እየቆዩ በጎን ወጥተዉ ወደ ማህበረሰቡ እየተቀላቀሉ መሆናቸዉን የተለያዩ ጥቆማዎች ደርሰዉናል፡፡

የጋራ ደህንነትን ለመጠበቅ ሲባል ይህንን አስከፊ እና አደገኛ ወረርሽኝ አስቀድሞ መከላከል እንዲቻል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በግለሰቦቹ ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመዉሰድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በተለያዩ ለይቶ ማቆያ ያላችዉ ሰዎች ለራሳችሁ እና ለህዝብም ደህንነት ሲባል ባላችሁበት ቦታ ለ 14 ቀናት በመቆየት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደረገዉ ጥረት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያሳስባል፡፡

ማህበረሰቡ በለይቶ ማቆያ የቆይታ ጊዜያቸዉን ሳይጨርሱ ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉትን ሲመለከት በአቅራቢያዉ ላሉት የህግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡

(የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top