Connect with us

ፖሊስ የአገልጋይ ዮናታንን ክስ አስተባበለ

ፖሊስ የአገልጋይ ዮናታንን ክስ አስተባበለ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

ፖሊስ የአገልጋይ ዮናታንን ክስ አስተባበለ

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪዲዮ የፖሊስ ተቋሙን የማይገልጽ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ ገለፁ፡፡

በከተማችን ሀዋሳ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በህገ መንግስቱ መሰረት የእምነት ነፃነታቸው ተጠብቆ በመሰረቱት በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያንም ሆነ በመልካም ወጣት ፕሮጀክት የሚያከናወኑት ተግባር ለወጣቶች ስብዕና ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ስራ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርም ሆነ ፖሊስ ተገንዝቦ በስራቸው ሁሉ ከጎናቸው በመሆን አስፈላጊ ድጋፍ በማድረግ ግዴታውን እየተወጣ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ሆኖም ግለሰቡ ጥቂት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አባላት ወከባ፣ ዛቻ እና ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊት ፈፅሞብኛል በማለት ቅሬታቸውን በህጋዊ መንገድ ከማቅረብ ይልቅ አጠቃላይ የቋማችንና የከተማውን አስተዳደር ስም በሚያጎድፍ ሁኔታ ቀስቃሽና በእምነቶች መካከል ልዩነት ያለ በማስመሰል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የለቀቁት መረጃ ተገቢነት የሌለውና ያሳዘናቸው መሆኑን ኮማንደር ኢዮብ በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

የጉዳዩ መነሻ የከተማ አስተዳደሩ ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል እየወሰደ ባለው እርምጃ መሰረት ከማክሰኞ ከለሊቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ረፉድ 4:00 ሰዓት የዋና ዋና መንገዶች ለፀረ-ተዋህሲያን ኬሚካል ርጭት ዝግ እንደሚደረጉ አስቀድሞ በተለያዩ ዘዴዎች መረጃው ለነዋሪዎች እንደተላለፈ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት የከተማችን ነዋሪዎች ለኬሚካል ርጭት ዝግ የተደረጉ መንገዶችን ባለመጠቀም ርጭቱ እንዲቀላጠፍ ሲተባበሩ የዋሉ ሲሆን ተግባራዊነቱን የሚከታተሉ የፖሊስ አባላት በተለያዩ አካባቢዎች ቁጥጥር እንዲያደርጉ መመደባቸውን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ግለሰቡ እንግልት ደረሰብኝ በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጩት መረጃ መሰረት ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት በእለቱ ግለሰቡ ለተሸከርካሪ ዝግ በተደረጉ መንገድ ላይ በመጠቀማቸው ምክንያት ለቁጥጥር ስራ ስምሪት ከወሰዱ የፖሊስ አባላት ጋር አለመግባባት መፈጠሩን ለማጣራት ችሏል። ጉዳዩንም በጥልቀት በማጣራት ችግር ፈጥረዋል የተባሉ አባላት ላይ ማስረጃ በመሰብስብ እርምት እንደሚወስድ አሳውቀዋል።

ከዚህ ውጪ ግለሰቡ በጥቂት አባላት ወከባ፣ ዛቻ ተፈፅሞብኛል በሚል ለሚመለከተው የህግ አካል አቤቱታቸውን ከማቅረብ ይልቅ መፍትሄ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፉት መልዕክት የተቋሙን አቋም የማይገልፅ፣ ስሙን የሚያጎድፍ እና ተገቢውን አካሄድ ያልተከተለ ብቻ ሳይሆን አሁን በሀገራችን በሶሻል ሚዲያ በሚለቀቁ መረጃዎች ምንም ሳያመዛዝኑ ወደ ችግር የሚገቡ በርካታ ወጣቶች ባሉበት ሁኔታ ቀስቃሽ መልዕክት ማስተላለፋቸው ከእርሳቸው የማይጠበቅ እንደሆነ ኮማንደር እዬብ ገልጸዋል።

ይሁንና ግለሰቡ ጥፋት ተፈጽሞብኛል ባሉት አጋጣሚ ቫይረሱን ለመከላከል እየተደረገ በነበረው ስራ ላይ ያደረጉትን አስተዋጾ ፖሊስ የሚያደንቅ ሲሆን ነገር ግን ማንኛውም አካል ፖሊስ ለሚያደርጋቸው የህግ ማስከበር ስራዎች ተባባሪ መሆን እንደሚገባውም ጠቁሟል ።

በአጠቃላይ ግለሰቡ ጥቂት የፖሊስ አባላት ጥቃት አድርሶብኛል ብለው የሚያቀርቡትን አቤቱታ የከተማው ፓሊስ ጉዳዩን መርምሮ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸው ነገርግን በህግ አግባብ ክስ መመስረት እየቻሉ፣ሐሚመለከተው ለመንግስት አካል አበቱታ ሳያቀርቡ በማህበራዊ ሚዲያ የለቀቁት መልዕክ ተገቢ ያልሆነና የከተማውን ፓሊስ ሰራዊት የማይወክል መሆኑን ኮማንደር እዬብ እሳውቀዋል።

በመጨረሻም ቫይረሱን ለመከላከል ለሚደረገው ርብርብ ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። (የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top