Connect with us

ትግራይ ክልል አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ

ትግራይ ክልል አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ትግራይ ክልል አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ

ትግራይ ክልል አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ

የትግራይ ክልል መንግሥት ባለፈው ሳምንት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት ካወጠው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት አንድ ወጣት በፖሊስ መገደሉ ተገለጸ።

ግድያው የተፈጸመው ናዕዴር አዴት በሚባል ወረዳ ውስጥ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር የማነ ኪዳነማሪም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ግድያው የተፈጸመው ቅዳሜ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም ናዕዴር አዴት ወረዳ ውስጥ ልዩ ቦታው ጅራ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን፤ ምክንያቱም በወጣው አዋጅ መሰረት ፖሊስ በመጠጥ ቤት ነበሩ ሰዎች እንዲበተኑ በማድረግ ላይ በነበረበት ጊዜ በተፈጠረ አለመግባባት እነደሆነ ተገልጿል።

ሟች ሃጎስ ንጉሥ የሚባል ወጣት እንደሆነና በአንድ የፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ወዲያው ህይወቱ ማለፉን የወረዳው ጽህፈት ቤት ሕዝብና የመንግሥት ግንኙነት ገልጿል።

በወጣቱ ግድያ የተጠረጠረው የፖሊስ አባልም በቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑንም የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ እረጋግጠዋል።

( ቢቢሲ )

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top