Connect with us

ዶ/ር አብርሀም የኮሮና መድሀኒት የመገኘት ተስፋ አስመልክተው ተከታዩን ብለዋል

ዶ/ር አብርሀም በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የኮሮና መድሀኒት በኢትዮጵያ የመገኘት ተስፋ አስመልክተው ተከታዩን ብለዋል
Photo Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ዶ/ር አብርሀም የኮሮና መድሀኒት የመገኘት ተስፋ አስመልክተው ተከታዩን ብለዋል

ዶ/ር አብርሀም በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የኮሮና መድሀኒት በኢትዮጵያ የመገኘት ተስፋ አስመልክተው ተከታዩን ብለዋል:-
***
‪ትላንት ኮረና ቫይረስ አስመልክቶ በኢትዮጵያዉያን ተመመራማሪዎች እየተካሄደ ያለውን ምርምር እና የደረሰበት ደረጃ አስመልክቶ በሰጠነው መግለጫ ፣እንዴት በኢትዮጵያውያን ይህ ሊሆን ይችላል በሚሉ ሃገራቸውን እነሱ የሚያውቁዋትን ያህል እውቀት ብቻ ያላት በሚመስላቸው እና ይህ ስራም ፖሊቲካዊ ገፅታ ሰጥተው፣ እኛ ያላወቅነው እንዴት ይሆናል በሚሉ አካላት ባልሆነ መንገድ ተርጉመው እያቀረቡ ያሉት ትርክት የለመዱትን የአሉባልታና የውሸት ዜና መስራት መቅረቱን ያልተረዱ እና ሀገራችን ለችግር ግዜ የሚደርሱ አዋቂዎችና ተመራማሪዎች እንዳሉዋት የማያውቁ ወይም ማወቅ የማይፈልጉ ሰዎች ናቸው እና የነሱ ማላዘን ይቀጥላል ሃገራችን እና ህዝቦችዋ ወደ ከፍታ ማማ ይጋዛሉ።

አሁንም በድጋሚ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ነገር የተጀመረው የምርምር ስራ እና እስካሁን የተገኘው ውጤት በጣም አበረታች ብቻ ሳይሆን በአጠረ ጊዜ ቀሪ ስራዎች በማጠናቅ ለህዝባችን የጀመረውን የምንጨርስ እና ያልነውን የምናድርግ መሆኑን እንደምናሳይ ነው።

የምርምር ቀሪ ስራዎች ማለትም የአኒማል ቶክሲስቲ እና ክልኒካል ቴስት ስራዎች በተፋጠነ መንገድ እየተሰሩ የሚገኘውን ውጤት ለህዝባችን እንገልፃለን።‬

‪የምርምር ቀሪ ስራዎች የራሳቸው ግዜ የሚወስዱ በመሆናቸው በዚህ መልካም ዜና ምክንያት በፍፁም መዘናጋት አይገባም አያስፈልግም በመንግስት የሚሰጡ የጥንቃቄ እርምጃዎች እንተግብር። ‬

‪ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦችዋን ይባርክ። ‬

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top