Connect with us

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
Photo Facebook

ዜና

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 87 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የመጀመሪያዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣ 2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች ተብሏል፡፡

ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በመጋቢት 19፣2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡

ሁለተኛ እና ሶስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡

ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻ ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top