Connect with us

አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በቀን 50 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እያመረተ ነው

አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በቀን 50 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እያመረተ ነው
Photo Facebook

ዜና

አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በቀን 50 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እያመረተ ነው

የአልመዳ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዳ በቀን በአማካይ 50 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እያመረተ መሆኑን አስታወቀ ።

ፋብሪካው ከኢትዮጵያ የምግብ የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ፍቃድና እውቅና ማግኘቱን ገልጸዋል።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለማሪያም ተስፉ ለኢዜአ እንደገለጹት ፋብሪካው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዳ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ከ12 እስከ 15 ብር በሚደርስ ዋጋ ለተጠቃሚው ለማድረስ እየሰራ ነው ።

ጭምብሉ ከሌላው ተመሳሳይ ምርት ለየት የሚያደርገው በፈሳሽ ሳሙና ደጋግሞ በማጠብ መልሶ ለአገልግሎት የሚውል መሆኑን ስራ አስክያጁ ተናግረዋል።

ፋብሪካው ለጊዜው በቀን 50 ሺህ ጭንብል በማምረት ላይ ሲሆን በቀጣይ የህብረተሰቡን የምርቱ ፍላጎት በማየት በሁለት እጥፍ ለማሳደግ እንደሚቻል አስረድተዋል ።

ምርቱን ለመግዛት የማይችሉ ታራሚዎችና ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች በነጻ እንደሚታደል ከፋብሪካው ስራ አስክያጅ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ኮማንድ ፖስት የፈጥኖ ደራሽ አስተባባሪ ዶክተር በረከት አረጋዊ በሰጡት አስተያየት ፋብሪካው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማምረት መጀመሩ ቫይረሱ በመከላከሉ ሒደት ጠቀሜታው የጎላ ነው ።

ምንጭ:- ኢዜአ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top