Connect with us

በአለም ላይ ፈጣኑ ወረርሽኝ ፍርሃት ነው‼️

በአለም ላይ ፈጣኑ ወረርሽኝ ፍርሃት ነው‼️
Photo Facebook

ጤና

በአለም ላይ ፈጣኑ ወረርሽኝ ፍርሃት ነው‼️

በ2002 እ.ኤ.አ ማርቲን ሪየስ የተሰኘ ወደረኛ ኮስሞሎጂስት አንድ ልተለመደ ውርርድ ይፋ አደረገ፡፡ እንዲህም ሲል፡- “BY 2020, BIOTERROR OR BIOERROR WILL LEAD TO ONE MILLION CASUALTIES IN A SINGLE EVENT/በ2020 በባዮ-ቴረር ወይም በባዮ-ኢረር በሚከሰት አደጋ በአንድዬ ብቻ 1 ሚሊዮን ህዝብ ይረግፋል።” ሲል ተወራረደ።

ፕሮፌሰር ስቴቨን ፒንክር ግን “እንዲህ አይነት ጥንቆላ ነክ ትንበያዎች እውን ቢሆኑ እንኳን የአለም መጨረሻ ናቸው ብላችሁ እንዳትሰጉ፤ የፍርሃት ወረርሽኝ እንዳይዛችሁ፤ ይልቁንም ጥንቃቄዎች የክፉ ቀን ትንቢቶች ማክሸፊያዎች ናቸው” የሚል መልዕክት ያለው “Enlignmenet Now” የሚል አወዛጋቢ መጽሃፍ ጻፈ፡፡

እ.ኤ.አ 2015 ላይ “የመጪው ዓለም ፈተና የኑክሊየር ቦንብ ሳይሆን የቫይረስ ቦንብ ነው” ብሎ ያስጠነቀቀው ቢሊየነሩና በጎ አደራጊው ቢል ጌት ሳይቀር የፒንከርን መጽሃፍ “የምንጊዜም ምርጡ መጽሀፌ” ብሎ አሞካሸለት፡፡

“የምክነያታዊ ተስፈኞች መጽሃፍ ቅዱስ” የሚል የዳቦ ስምም የተሰጠው የፕሮፌሰር ስቴቨን ፒንከር ተስፋ ሰጪ መጽሀፍ በኒው ርክ ታይም የዓመቱ መቶ ከፍተኛ ዋጋ ካላቸው መጸሃፍት ውስጥም አንዱ ነው፡፡

ፕሮፌሰር ስቴቨን ፒነከር በሀርቫርድ ዩኒቨርሰቲ የሥነ-ልቦና ፕሮፌሰር ነው፡፡ ደፋርና ተስፈኛ መልዕክቶችን በያዙ መጻህፍቱ፣ ንግግሮቹና ጥናቶቹ የፑልቲዘር ሥነጽሁፍ ሽልማትን ጨምሮ አያሌ ሽልማቶችን አጋብሷል፡፡ የታይም መጽሄት መቶ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና የፎሬይን ፖሊሲ መቶ ግንባር ቀደም አሰላለሳዮች(leading thinkers) መካከልም አንዱ ነው፡፡

ቢል ጌትስ ስለ ፕሮፈሰር ፒንከር እሳቤ እንዲህ ይላል። “The world is getting better, even if it doesn’t always feel that way. I’m glad we have brilliant thinkers like Steven Pinker to help us see the big picture. Enlightenment Now is not only the best book Pinker’s ever written. It’s my new favorite book of all time.”

ፕሮፌሰር ፒንከር በአብዛኛው መልዕክቶቹ በምክኔታዊ አወንታዊነት እና አብርሆት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ አለም ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለችና ለአብርሆት ትሩፋቶች እጇን እየሰጠች ነው ብሎ ያሰላስላል፡፡ ነገር ግን አሁንም የሰው ልጆችን ህልውና ሚፈታተኑ አያሌ ተግዳሮቶች እንዳሉ አምነን እንደ አለም መጨረሻ ሳይሆን ልንፈታቸው እንደምንንችላቸው ችግሮች ማየት መቻል አለብን ይላል፡፡ ““But we can treat them not as apocalypses in waiting but as problems to be solved.”

የዛሬ መቶ አመት ገደማ በ1918 (እ.ኤ.አ) ተቀስቅሶ በመላው አለም 50 ሚሊዮን ሰዎችን የፈጀው በተለምዶ ስፓኒሽ ፍሎ ተብሎ የሚጠራው ወረርሽኝ በአሁኑ ጊዜ ቢከሰት ኖሮ ከአስር ሺዎች የዘለሉ ነፍሶችን ባልነጠቀን ነበር ብሎም ይቆጫል፡፡

ፕሮፌሰር ፒነከር ይሄንን ለማለት በቂ ምክነያቶች አሉኝ ባይ ነው፡፡ “የዛሬ 500 አመት ገደማ ጀመረው ኢንላይትመንት (አብርሆት) ንቅናቄ አመክንዮን፣ ሳይንስን፣ ምርምርንና ግኝትን እያሳደጎ ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊከሰቱብን የሚችሉ እንደወረርሽኝ ያሉ ፈተናዎችን ብዙ ጥፋት ሳያደርሱ መቋቋም እንችላለለን፤ በአለም ላይ ያሉ ታላላቅ ላቦራቶሪዎች በሰው ልጆች ላይ ጥፋት የሚጠነሰስባቸው ማድጋዎች የሆኑትን ያህል ማርከሻውም ከዚያው ከሳይንስ አቁማዳ የሚሰፈር መሆኑ ምክነያታዊ ተስፋን ያላብሳል” ብሎም በማስረጃና በመረጃ አስደግፎ ይከራከራል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አለም የደረሰችባቸው የክትባትና የመድሃኒቶች ግኝት ፍጥነት፣ የመረጃ ዝውውር፣ አለም አቀፋዊ ትብብርና የተሻለ የህክምና አገልግሎት በመኖሩ ብቻ በዚህ ዘመን የሚከሰት ወረርሽኝ የሚፈራውን ያህል ጉዳት ሊደርስ አይችልም ብሎም ይወራረዳል፡፡
`
“Sowing fear about hypothetical disasters, far from safeguarding the future of humanity, can endanger it.” Steven pinker
የተንሸዋረሩ የዜና ሽፋኖች፣ የተዛቡ መረጃዎችና ፖለቲካዊ ደባ የተጣባቸው ፕሮፓጋንዳዎች የሚነዙት የፍርሃት ወረርሽኝ ሰዎችን የመከላከል አቅም ከማሽመድመዳቸውም በላይ ከወረርሺኙ በኋላ ለሚመጡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችም ዳፋቸው ይተርፋል፡፡

አዕምሯችን በፍርሃት በሚወረርበት ጊዜ ሆርሞኖቻችን ግራ በመጋባት ሞድ(alteted mode) ላይ ስለሚሆኑ የሰውነታችን በሽታ መከላከያ ስርዓት ሃይሉን በእጅጉ ያጣል፡፡ ከፍተኛ ፍርሃት ከተቆጣጠረንም ተስፋ ስለምንቆርጥ ( አሁን አኛ ሃገር እንደሚታው) ጥንቃቄ ለማድረግ ጉልበት አናገኝም፡፡ በዚህም የተነሳ የፈራነው ይደርስብናል፡፡ የደረሰብንም ያጠፋናል፡፡

በሽታው ከገደላቸው ይልቅ የበሽታው ፍርሃት የሚገድላቸው በአያሌው ሊበልጡ ይችላሉ፡፡ “And the more ways people can imagine bad things happening, the higher their estimate that something bad will happen.” ሲልም ለጥፋት ሰባኪዎች ሟርት መሳካት በኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይችላልና “STOP TELLING EVERYONE DOOMED!” ይላል ፕሮፌሰሩ፡፡

ስለሳይንስ ተስፋ፣ ስለሰው ልጅ ህልውና አደጋዎች፣ ስለድህነትና ብልጽግና፣ ስለ መጪው ጊዜ ገዢ ሃሳቦችም ብዙ ብዙ ሚለው አለው፡፡ መጽሃፉ አሁን በሀገራችን በገበያ ላይ ይገኛል፡፡ ቢያነቡት ዘመኑን ይዋጁበታል። ፍርሃቱን ቀነስ ጥንቃቄውን ጨመር አድርገው ዘና ይበሉ፡፡ #ተስፋ አለን! #በእርግጥም እናሸንፈዋለን!

“But apocalyptic thinking has serious downsides. One is that false alarms to catastrophic risks can themselves be catastrophic.”
Be more informed and less panicked!

ለበለጠ መረጃ ወይም መጽሃፉን ለማግነት 0911124036 ወይም 0961004364 ላይ ይደውሉ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top