Connect with us

የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ
Dr. Catherine Hamlin, right, at the Addis Ababa Fistula Hospital in Ethiopia in 2008.Credit...Kate Geraghty/Sydney Morning Herald, via Getty Images

ዜና

የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

የኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል መሥራች የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የተከናወነው የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በመኖሪያ ቤታቸው የአስከሬን ሽኝት ከተደረገ በኋላ ነው።

ከመሐንዲስ አባት እና ሐሳብ አፍላቂ እናት የተወለዱት ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ለቤተሰባቸው ሁለተኛ ልጅ ነበሩ።

ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን በፌስቱላ ሕመም ተጠቂ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላበረከቱት እጅግ ከፍተኛ የሆነ የበጎ አድራጎት የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።

ዶ/ር ካትሪን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 ዓመታት በላይ ለ60 ሺህ ያህል ሴቶች የፌስቱላ ሕክምና ሲሰጡ ነበር።

ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top