Connect with us

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምንት እርምጃዎችን ይፋ አደረጉ

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምንት እርምጃዎችን ይፋ አደረጉ
Photo: Facebook

ጤና

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምንት እርምጃዎችን ይፋ አደረጉ

1. ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም አንስቶ፣ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰው የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎች የሚያስቆም እና ማሕበራዊ ርቀትን መጠበቅን የሚያስተገብር ይሆናል።

2. የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ፣ የመንግሥት ተቋማት ርቀትን ተፈጻሚ ማድረግ እና ስብሰባን ሲያካሂዱ ቫይረሱን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው።

3. የመንግሥት ተቋማት የተቀጣሪዎቻቸውን ሁኔታ በማጣራት እንደየሁኔታው አንዳንዶች በቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን መንገድ ማመቻቸት።

4. የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች አጨናንቆ ተሳፋሪዎችን መጫን የማይችሉ ሲሆን፥ ይህን ማድረጋቸው በትራፊክ ፖሊስ እና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ቁጥጥር የሚደረግበት ይሆናል።

5. ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት እና ፖሊስ ውስጣዊ ቅድመ ዝግጀት በማካሄድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቫይረሱን ስርጭት የመከላከል ሥራን ለማስፈጸም መዘጋጀት።

6. በተጠቃሚው ማኅበረሰብ ላይ ሕገ ወጥ የዋጋ ጭማሪን የሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚቀጥሉ ይሆናል።

7. መገናኛ ብዙሀን በትኩረት በየደረጃው ግንዛቤን የማሳደግ ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል።

8. ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ይገታል። ይህ እርምጃ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦችና አስፈላጊ መገልገያዎችን አይጨምርም።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top