Connect with us

‹ ህወሓት ያበቃለት ድርጅት ነው› – አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል

‹ ህወሓት ያበቃለት ድርጅት ነው› – አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
Photo Facebook

ፓለቲካ

‹ ህወሓት ያበቃለት ድርጅት ነው› – አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል

ህወሓት በትግራይ ህዝብ ታቅፎ ያለው የተሻለ ሀሳብ ኖሮት የተሻለ ስራ ስለሰራ ሳይሆን የተበላሸ አካሄድ ስላለ ነው፡፡ ያ የተበላሸ አካሄድ ደግሞ እስኪስተካከል ድረስ በጊዜያዊነት የተፈጠረ መግባባት ነው እንጂ ህዝቡ ከህወሓት አገዛዝ መላቀቅ እንደሚፈልግ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የብልፅግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ገለፁ።

ህዝቡ እየጠበቀ ያለው የለውጡ ሂደት ሰከን እስኪል ድረስ ነው ያሉት ኃላፊው ህዝቡ ሰከን ባለበት ሁኔታ የሚጠብቀውም ሌላ አጀንዳ መጨመርም ተገቢ አይደለም በሚል የትግራይ ህዝብ ነገሮችን በጥሞና እየተከታተለ ነው ብለዋል።

አያይዘውም “ህወሓት ከዚህ በኋላ ሀሳብ ማመንጨት የሚችል ፓርቲም አይደለም። የትግራይ ህዝብም ህወሓትን መጠየቅ የሚፈልገው ብዙ ጥያቄ አለው። ምክንያቱም ከሌላው ህዝብ በላይ የትግራይ ህዝብ በህወሓት ተበድሏል። የሴራ ፖለቲካ ሰለባ እየሆነ ቆይቷል። ስለዚህ አሁን ህወሓት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት ያለው የሚመስለው በሴራ ፖለቲካና ፕሮፖጋንዳ ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ በራሱ ሰዓት መስራቱን ያቆማል” ማለታቸው ተዘግቧል።

እንደአቶ ነብዩ ገለፃ ኢትዮጵያ ህዝብን በማጠልሸት ያልተፈጠሩ ግጭቶችን የተፈጠሩ በማስመሰል መኖር አይቻልም። በተለይም በዚህ ዓመት ፕሮፖጋንዳው የትግራይ ህዝብን ማስተዳደር አይችልም፤በመሆኑም አሁን ላይ ሁሉም ነገር ያለቀለት ነው።

“ህወሓት ከዚህ በኋላ ለትግራይ ህዝብ አማራጭ ሆኖ መቀጠል አይችልም። በሀሳብም በአደረጃጀት፣ በባህሪም ሆነ በሌሎች ጉዳዮችም ከትግራይ ህዝብ ጋር የማይሄድ እንደውም የህዝቡን ገጽታ ያጠለሸ ነው። በብዙ መልኩም አሁን ላይ ፈርሷል፤

ህወሓት ያለቀለት ደርጅት ነው፤ ስለዚህ አማራጭ ሊሆን አይችልም፤ ከዚህ በኋላም ታሪኩ እንዴት እንደሚወሳ ነው መጨነቅ ያለበት። ጉዞውም በጣም ረዥም ነው፤ ከ60 ዎቹ ተነስቶ እስከ አሁን ልቀጥል ማለት አንዱ የውድቀቱ ምንጭም ነው።

አሁን ላይ ሀሳብ ስለሌለው መዋጋት የሚፈልገው በሌላ መልኩ ሊሆን ይችላል። ግን እሱም ቢሆን ከፍተኛ ተጠያቂነትን የሚያመጣና ለትዝብት የሚዳርግ ነው። እኛው ከዚህ በፊት የተፈጸሙትን የስም ማጥፋትና ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ፍትህ እንዲሰፍን ከፍተኛ የሆነ ትግል እናካሂዳለን።

አዲስ የወጣት አደረጃጀት በብልጽግና ፓርቲ አማካይነት መጥቷል፤ እስከ አሁንም ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴን እያደረገ መጥቷል የትግራይ ህዝብም ይህ ፓርቲ የኔ ነው ብሎ ማመን የጀመረው ከመጀመሪያ ጀምሮ ነበር።

ከፕሮፖጋንዳው ባሻገር የህዝቡ እውነተኛ ስሜትን መመልከት የሚቻልበት እድልም አለ። እናም ፕሮፖጋንዳው ለጊዜው የተፈጠረ ምናልባት በዚህ ፕሮፖጋንዳ የተሸወደም ካለ ለእሱ ትክክለኛውን መንገድ ማሳየትና ለውጡም በትክክለኛ መስመር ላይ እንዳለ እናሳያለን። ትልቁ ነገር የሚሰማ እውነትን የሚፈልግና ፍትህ የናፈቀ ህዝብ አለን።

አሁን የተፈጠሩት አንዳንድ ሁኔታዎች በአጭር ጊዜ ተቀይረው በአገር ደረጃ የመጣውን ለውጥ ከጫፍ እስከጫፍ ለማድረስ እንሰራለን። ይሄም እውን ይሆናል” ሲሉ አቶ ነብዩ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top