Connect with us

ሰብዓዊነት ይቅደም…!! ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)

ሰብዓዊነት ይቅደም...!! ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ሰብዓዊነት ይቅደም…!! ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)

ሰብዓዊነት ይቅደም…!! ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር መልዕክት)

ኢትዮጵያውያን ከጀግንነታቸው ትይዩ ወደር የማይገኝለት ሰብዓዊነትም መገለጫቸው ነው፡፡ በተለይም ከጥንት እስከ ዛሬ በሰው ልጆች ላይ አንዳች ፈተና ሲመጣ አንዱን ከሌላው ሳይለዩ በአገራቸው ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት ዘምተው ለሰዎች ደህንነት ራሳቸውን አሳልፈው እስከመስጠት መድረሳቸው ሲታይ መሠረታቸው ሰብዓዊነት፣ መገለጫቸው እውነተኛ ፍቅር መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

እንደሚታወቀው በአሁኑ ጊዜ ዘር፣ ቀለም፣ እድሜ፣ መልክዓምድርና መሰል ጉዳዮች ሳይገድቡት ዓለማችንን እያስጨነቀ ያለው የኮሮና ቫይረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም እና ለህልፈተ ህይወት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ይህ በሽታ በዓለም ዙሪያ መስፋፋቱንም አላቆመም፡፡ በቅርቡም በአገራችን በበሽታው የተጠቁ ወገኖች ተገኝተዋል፡፡

ታዲያ የአገሬ ልጆች እንዲህ ባለ ፈታኝ ወቅት “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” በማለት ቅን ሰዎች ለሰው ልጆች ያለ አድልዎ ድጋፍ በሚያደርጉባት አገር የምንገኝ፣ የካበተ የመረዳዳት፣ የመደጋገፍና የፍቅር ባህል ያለን እንደመሆኑ ይህንኑ ነባር ባህላችንን በተግባር በመግለጽ እናሳይ እላለሁ፡፡

በተለይ ወደ አካባቢያችን የሚመጡ የአገር ውስጥም ይሁን የውጭ አገር እንግዶች የተለየ አክብሮትና እንክብካቤ በማድረግ ሰብዓዊነታችንን በግልጽ እናስመስክር፡፡ በሽታ ድንበር ስሌለው ኢትዮጵያዊ የሆኑም ሆነ ያልሆኑ ወገኖቻችንን ፍቅር፣ አክብሮትና እንክብካቤ አንንፈጋቸው እላለሁ፡፡ ባለማወቅ ከዚህ ባህል የወጣ ሥራ የሚፈጽም ካለም በመምከርና በመገሰጽ ዓርዓያ እንሁን፡፡

ሰዎች እንዲሳቀቁብን ሳይሆን እንዲመኩብን በማድረግ የቅን ኢትዮጵያውያን ልጆች መሆናችንን በተግባር እናሳይ፡፡ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የሚያስተላልፉትን የጥንቃቄ መልዕክት ተግባራዊ ማድረግ እንቀጥል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top