Connect with us

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለ15 ቀን የታራሚዎችን ቤተሰብ ጥየቃ ማገዱን አስታወቀ

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለ15 ቀን የታራሚዎችን ቤተሰብ ጥየቃ ማገዱን አስታወቀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለ15 ቀን የታራሚዎችን ቤተሰብ ጥየቃ ማገዱን አስታወቀ

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአገሪቱ ከተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ታራሚዎችን ለመጠበቅ ሲባል ለመጪዎቹ 15 ቀናት ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግድ መጣሉን አስታውቋል።

የማረሚያ ቤቱ ጄኔራል ኮሚሽነር ጀማል አባስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ክልከላው ለመጪዎቹ 15 ቀናት ይቆያል።

ታራሚዎች የከፋ የጤና ችግር ካልገጠማቸው በስተቀር ወደ ሆስፒታሎች በሪፈራል እንደማይላኩም ገልጸዋል።

አስተዳደሩ በማረሚያ ቤቶች አካባቢ ሊከሰት የሚችለውን ችግር ቀድሞ በመለየት ለመከላከል ሂደቱ የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መግባቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ስድስት ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት መካከል አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት በማቆም በደህና ሁኔታ ላይ ሲገኙ፤ ቀሪዎቹ ሁለት ታካሚዎች ከህመሙ በማገገም ላይ መሆናቸውንና የቅርብ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ትናንት መግለጹ ይታወቃል።

ኢዜአ | መጋቢት 10/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top