Connect with us

ኢትዮጵያዊው የበጎ አድራጎት ሰው በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በስማቸው ሕንጻ ተሰየመላቸው

ኢትዮጵያዊው የበጎ አድራጎት ሰው ክቡር ዶክተር አዳሙ አንለይ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በስማቸው ሕንጻ ተሰየመላቸው

ባህልና ታሪክ

ኢትዮጵያዊው የበጎ አድራጎት ሰው በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በስማቸው ሕንጻ ተሰየመላቸው

ኢትዮጵያዊው የበጎ አድራጎት ሰው ክቡር ዶክተር አዳሙ አንለይ ለደቡብ ጎንደር ዞን ለአማራ ክልልና ለሀገራቸው በሰሩት ስራ ይዘከሩ ዘንድ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንዱን ሕንጻ በስማቸው ሰየመ፡፡

ክቡር ዶክተር አቶ አዳሙ አንለይ ሂውማን ብሪጅ በሚባል የሀገረ ሲውዲን ግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ የኢትዮጵያና የአፍሪቃ ዳይሬክተር ሆነው የሚሰሩ ሲሆን ሀገራቸው ኢትዮጵያ በህክምና ቁሳቁሶች እጥረት ያለባት ችግር ይቀረፍ ዘንድ እጅግ በርካታ አርባ ጫማ ኮንቲነሮችን በስጦታ እያስመጡ ያበረከቱ ናቸው፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ክቡር ዶክተር አዳሙ አንለይ በዜግነት ሲውዲናዊ ቢሆኑም ሀገራቸውን የሚወዱ በርካታ ስጦታዎችን በመለገስ ስማቸው የገነነ ሲሆን በሀገራችን ለሚገኙ በርካታ ሆስፒታሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ለግሰዋል በዚህም ለአዲግራት መቐለ ሀይደር ሪፈራል ሆስፒታል፣ ለጅግጅጋ፣ ለተለያዩ የደቡብ ክልል ሆስፒታሎች፣ ለደብረ ማርቆስ፣ ጎንደር፣ ደባርቅ፣ ባህር ዳር፣ ጅማ፣ አሰላ፣ አዳማና ሻሸመኔን ጨምሮ በርካታ ሆስፒታሎችን በሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን በድጋፍ የለገሱ ናቸው፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲም የበጎ አድራጎቱ ሰው በዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አቀፍ ግዛቶች ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እውቅና ሰጥቷል፡፡ በእኚህ በጎ አድራጊ ግለሰብ በኩል ጋይንት፣ አርብ ገበያ ጤና ጣቢያ፣ ስማዳ፣ ወለላ ባህር ጤና ጣቢያ፣ እብናት፣ ወግዲ፣ ንፋስ መውጫና ደብረ ታቦር ሆስፒታሎች የህክምና ቁሳቁሶችን አግኝተዋል፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ክቡር ዶክተር አዳሙ አንለይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በደብረ ታቦር ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኝ የማስተማሪያ ሕንጻ “አዳሙ አንለይ ሕንጻ” ተብሎ እንዲሰየም ወስኗል፡፡

አቶ አዳሙ አንለይ በ2011 ዓ.ም. የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ለዚሁ አገልግሎታቸው የክብር ዶክትሬት ያበረከተላቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top