Connect with us

ከትከሻችን ውረዱ!

ከትከሻችን ውረዱ!
Photo : Facebook

ኢኮኖሚ

ከትከሻችን ውረዱ!

ከትከሻችን ውረዱ! | (አሥራት በጋሻው)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ:- እነ እንቶኔ ከጀርባችን ውረዱልን። ይህ ጊዜ ከእናንተ ጋር አፍ የምንካፈትበት ሳይሆን እንዴት ከዚህ ፈተና የምንወጣትን ዘዴ የምናሰላስልበት እና ጠንክረን የምንሰራበት ነው።

ክፉ ማሰብ እና ያልሆነውን እና ያልተፈጠረውን ማሰላሰል ከድካም በስተቀር የሚያስገኘው ነገር የለም። የስራ ማቆም አድማ ለጠራችሁም ሰሚ አታገኙም።

ሰራተኛው ሀገሩን እና መስሪያ ቤቱን እንዴት እንደሚወድ ለማታውቁ እንደ መንደሩ ስጋ ቤት ረቡእ ዘግታችህ ሐሙስ ከፍታችሁ የምትሰሩበት አይደለም ።

ዛሬ አለም በደረሰበት ቴክኖሎጂ ደረጃ ዘምኖ ከአለም ተወዳድሮ የሚሰራ እንጂ በዘፈቀደ እነ እንትና ስላሟረቱ የሚከስር ወይም እነ ወፍ አንግስ ስለ በጠረቁ የሚወድቅም አይደለም።

ከአየር መንገዱ ሐላፊዎች ትከሻ ወረደህ ተገኝና እንተያይ። ያኔ ሲስተሙ ላይ ትወድቃለህ ከኔ ጋር ግጭት ትጀምራለህ። 15ሺ ሠራተኛ ውሎ ከሚገባበት ከ40ሺ በላይ ዙሪያውን ከበው አብረውት ከሚውሉ ወጥቶ አደሮች ጋር በሰፊው ሜዳ እንላተማለን። ያኔ ትግላችን ሞት ከሚደግሱልን ንፍሮ ከሚቀቅሉልን ጋር ይሆናል ።
የፈለከውን በል ሲስተሙን አትንካ። ሲስተሙን በተራ ምሳሌ ማስረዳት ይከብደኛል ።

እንግሊዘኛው ሲስተም ስልህ ቃል አልገልጽልህ ብሎኝ እንጂ ውስጤ የሚነግረኝ እነዛ ቀደምት የሙያ አባቶች ያስረከቡንን መንገድ ማለቴ ነው። ነጮቹ ጥቁሮቹ ኢትዮጵያውያን አይችሉም ብለው የበረራ አስተናጋጅ ከግሪክና ህንድ ያስመጡ ቀን
በውስጣቸው የተሰማቸውን አንጀት የሚያሳርር ስሜት ችለው የማስተዳደር ብቃት እንደሌላቸው መርዶአቸው የተነገራቸው ቀን የተሰማቸውን ስሜት ተቋቋመው እንዴት ለዛሬዋ ቀን እንደደረስን ሳስብ ነው። አየር መንገዱ እኔ አንተ በምናስበው ደረጃ ሳይሆን ለአፍሪካውን ኩራት ለኢትዮጵያውያን መመኪያ ነው። የሰባ አራት አመት ጎልማሳ።

ይህ ሁሉ ፋከራ ተውና ለኮሮና -19 ብቻ መፍትሄ ይሁን እንደሆን በረራ አቁሙ ከሆነ በረራም ስራም አይቆምም። በረራ ማቆም መብራት አጥፍቶ እንደመተኛትም ቀላል አይደለም።

በበሽታው ምክንያት የአለም የጤና ድርጅት የጉዞ ማእቀብ አላደረገም። ሌሎችም ሀገራት በተናጠል ውሳኔ ድንበራቸውንና የአየር ክልላቸውን ዘግተዋል። ለዚያ ደግሞ እኛ የተንደላቀቅን አይደልንምና አላደረግነውም። ለኒውክሊየር ባለቤቶችም ሆነ ለምስክኒዎቹ በሽታው ምህረት አያደርግም። እንደ እኛ አይነቱ የድሀ ድሀ ህዝብ ከአለም ተገልለን ለአንድ ለሊት ማደሩ አይሆንልንም።

አምላኩን የሚተማመነው ድሀ ህዝባችን ተጨማሪ መከታ የሆነው ዘንድ ብቸኛው ወደቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።
ይህ ጊዜ የአየር መንገዱን ሠራተኞች አንድ የሚያደርግ እንጂ የሚያለይይ አይደለም። በአንድ ልብ መክረው በአንድ ልብ መስክረው ክፋውን የፈተና ጊዜ ያልፉታል ።

ድርጅቱም በየዘመኑ ከገጠሙት ፈተናዎች አልፎ እንደተለመደው በውጤት እንደሚወጣ አልጠራጠርም።በሽታውም ይጠፋል።
እንደ ሀገርም አብረን እንበለጽጋለን ።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top