Connect with us

የፊት ማስክ በ500 ብር እንሸጣለን በማለት ሲያስተዋውቁ የተገኙ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የፊት ማስክ በ500 ብር እንሸጣለን በማለት ሲያስተዋውቁ የተገኙ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የፊት ማስክ በ500 ብር እንሸጣለን በማለት ሲያስተዋውቁ የተገኙ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ውስጥ ‘የፊት ማስክ በ500 ብር እንሸጣለን’ በሚል በማህበራዊ ድረ ገጽ ያስተዋወቁ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአራዳ ከፍለ ከተማ ፓሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪቹ ህገ-ወጥ መድሃኒቶችን ለመድሃኒት ማስቀመጫና መሸጫ በተከለከለ ቦታ ይዘው ተገኝተዋል።

የወንጀል መርማሪ ምክትል ሳጂን አዳነኝ አዱኛ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በማህበራዊ ትስስር ገጽ /ፌስ ቡክ/ በተጋነነ ዋጋ ‘የፊት ማስክ እንሸጣለን’ ብለው በለጠፉት ማስታወቂያ ነው።

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ከከተማው አስተዳደር ግብረኃይል ጋር በቦታው ተገኝቶ ለማረጋገጥ ሞክሯል።

ነገር ግን በወቅቱ የፊት ማስኩ ተሽጦ እንዳለቀና ሌሎች መድሃኒቶች እንዳሏቸው የገለጹላቸው ሲሆን ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድሃኒት በግለሰቦቹ መጋዘን ተገኝቷል።

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ስሙ ገተር ህንጻ አካባቢ መሆኑን ፖሊስ ጠቁሟል።

እነዚህ ግለሰቦች የፊት ማስኩን በተጋነነ ዋጋ ከመሸጥ ባለፈ ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠና የጸጉር ማሳደጊያ ነው የተባለ መድሃኒት በ3 ሺህ ብር ሲሸጡም ተገኝተዋል።

ፓሊስ ተጠርጣሪዎቹን ከማስረጃዎች ጋር በመያዙ ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ምክትል ሳጂን አዳነኝ ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ምንም ዓይነት የንግድ ፈቃድና ደረሰኝ በእጃቸው አለማግኘቱንም አስታውቀዋል።

ኢዜአ |  መጋቢት 07/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top