Connect with us

“እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና፤”

"እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና፤"

ባህልና ታሪክ

“እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና፤”

“እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና፤”

(ኦሪት ዘጸአት ፩፭፣፳፮)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የሩቅ ምሥራቅ ሀገራት ሀገረ ስብከት፤ በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተለይ በሀገረ ስብከታችን በቻይና፣ በኮሪያ፣ በጃፓንና እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ሁሉ በደረሰው ሞት ምክንያት የተሰማንን ኀዘን እየገለፅን- የምሕረት አምላክ፤ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ዘላለማዊ ቸርነቱ፣ ፍቅሩና ርኅራኄው ለምድራችን ፈጥኖ ፈውስን፣ መድኃኒትን እንዲያደርግ በቀንና በማታ በጸሎት እያሰብናችሁ መሆናችንን ለመግለፅ እንወዳለን።

ቅዱስ መጽሐፍ፤ “ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፤ ማስተዋል ይጋርድሃል።” እንዲል- (ምሳሌ ፪፤፲፩)፤ በሕክምና/በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ራሳችንንም ሆነ ሌሎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ይህን ወረርሽኝ በመከላከል ሓላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ እንላለን።

እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላችኋለሁ፥ እፈውሳቸውማለሁ፤ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ። (ኤር. ፴፫፤፮)።

የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በፍቅር፣ ሰላምና በጤና ይጠብቃችሁ! የእመቤታችን፣ የእናታችን፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና የቅዱሳን ጸሎት አይለየን!

አባ ያዕቆብ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሩቅ ምሥራቅ ሀገራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በዩኒቨርሳል ሰላም ፌዴሬሽን የዓለም ሰላም አምባሳደር።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top