Connect with us

“በገዳም ስም የሚመጣ ነጋዴ የተረገመ ነው፡፡” – ከስናፍቅሽ አዲስ

"በገዳም ስም የሚመጣ ነጋዴ የተረገመ ነው፡፡" - ከስናፍቅሽ አዲስ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“በገዳም ስም የሚመጣ ነጋዴ የተረገመ ነው፡፡” – ከስናፍቅሽ አዲስ

“በገዳም ስም የሚመጣ ነጋዴ የተረገመ ነው፡፡”
ገንዘብ አለኝ ብሎ ተስገብግቦ የሚሸምት ዋጋ አንሮ የሚሸጥን ጅብ ነጋዴ ያኽል የትውልድ ጠላት ነው፡፡
****
ከስናፍቅሽ አዲስ
ሰሞኑን ከገዳም መጣች የተባለችዋ መልእክት የፌጦ ዋጋ ሲንር ማን እንደአቀነባበራት ደረስንባት፡፡ ነጭ ሽንኩርት የእጥፍ እጥፍ ሲሆን የገዳሟ መልእክት የአባቶች ሳትሆን የጅቦች መሆኗን አወቅን፡፡ የገዳም አባቶች እንዲህ ያለ አድካሚ ግብ የላቸውም ፈውስን ከሰማይ ይለምናሉ እንጂ፤

በገዳም ስም የሚመጣ ነጋዴ የተረገመ ነው፡፡ መጀመሪያ ስቶክ ያከማቻል፤ ያከማቸውን በውድ ዋጋ ለማጣራት ገዳም መርጦ አወዛጋቢ መልእክቶችን በሽርክ ተከፋዮቹ በኩል ያዳርሳል፡፡ የዋህ ይሄን ያስተጋባል፤ ገብጋባ በርሮ ሱቅ ይደርሳል፡፡ ዋጋ ሳይጠይቅ አምጣ ብሎ ያግበሰብሳል፡፡

ሰሞኑን ሸዋ ሱፐር ማርኬት የቻልኩትን አቀርባለሁ ግን የሚያስፈልጋችሁን ብቻ ግዙ ብሎ የነጋዴን ሐጢአት የሚደመስስ መልካም ተግባር አሳይቶናል፡፡ እንዲህ ላለው ገብጋባ ሲሳይ የሚያደርገን ስስታችን ነው፡፡ ከሚያስፈልገው በላይ የሚሸምት ስግብግብ ገዢ ሆዳም ብለን ከምንወቅሰው ጅብ ነጋዴ ያልተለየ ነው፡፡

ዋጋ የሚንረው የታወረ ፍላጎት ሲበዛ ነው፤ አስር ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ገዝቶ መሄድ መድሃኒት ከመፈለግ ያለፈ ችጋር ነው፡፡ ችጋር ችጋራሞችን ክፉ ያደርጋል፡፡ ችጋራሞች ምን ቢበሉ ሆዳቸው ጥልቅና ከርስ ነው ሁሌም የሰው አጥንት ይግጣሉ እንጂ ወገን ካለ ነው የምንኖረው አይሉም፡፡

ጤና ሚኒስትር የተሰጠው ረዘም ያለ የዝግጅት ጊዜ አልተጠቀመበትም፤ እንድንዘጋጅ አልነገረንም አልኮል እንኳን በበቂ ሁኔታ የነጋዴን ክፉ ምኞት በሚያከሽፍ አግባብ አቅርቦ መጠበቅ አልቻለም፡፡

የፌት ማስክ በቢቂ ሁኔታ አዘጋጅተን የምንጠብቅበት በቂ ጊዜ ነበረን ግን እዚያም ውስጥ ነጋዴ የገዛቸው ሆዳሞች ሳይኖሩ አልቀረምና ተንከርፎ ጠበቀ፤ የዚህ ውጤት ተዳምሮ የገዳም አባቶች ጭምር አሉ እያለ ትርፍ ማጋበስ የሚሞክር የሞት ነጋዴ ስልቱን እየቀያየረ አለ፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top