Connect with us

የበጎ ሰዎች ምግባር

የበጎ ሰዎች ምግባር
Photo: Aschalew Getachew

ባህልና ታሪክ

የበጎ ሰዎች ምግባር

#የበጎ_ሰዎች_ምግባር

“ሰው ማለት

ሰው ማለት

ሰው የሚሆን ነው

ሰው የጠፋ ዕለት”

ነገሩ እንዲህ ነው…

በሐዋሳው የሆቴልና ቱሪዝም መድረክ ላይ አንዲት ሴት ሳግ እየተናነቃቸው ብሶታቸውን፣ ጉዳታቸውን መንግሥትና ሕዝብ ይወቅልኝ ብለው ተነፈሱ፡፡ ወ/ሮ ሣራ አሕመድ በሰው ሐገር ደክመው ያፈሩትን ሰንቀው ሀብት ሐረር ላይ ሐኪም ሎጅ በመገንባት ለቱሪዝም ኢንደስትሪ የበኩላቸውን እየጣሩ በነበረበት ወቅት ያልታሰበ አደጋ ገጠማቸው፡፡ በሐረር ከተከሰተው ረብሻ ጋር ተያይዞ የገነቡት ሎጅ እና ለውጭ ገበያ ያዘጋጁት አንድ ኮንቴነር ቡና በእሳት ወደመ፡፡ ጠንካራዋ፣ ታታሪዋ ሴት በክፉዎች የጭካኔ ምግባር አጨብጭበው ቀሩ፡፡ የሩቅ ሕልማቸው ጨነገፈ፡፡

ሴትየዋ ሳግ እየተናነቃቸው ጉዳታቸውን በተናገሩበት መድረክ ያልታሰበ ሲሳይ መጣ፡፡ አቶ ወርቁ አይተነው 10 ሚሊዮን ብር ፣ ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ የወ/ሮ ሣራን እምባ አበሱ፡፡ በእነሱ ወገናዊ ድጋፍም የወ/ሮ ሣራ ተስፋ መልሶ እንዲያንሰራራ ሆነ፡፡

አቶ ወርቁ ከሰጡት ብር በላይ በመድረኩ ያደረጉት ንግግር ለብዙዎቻችን የሚሊዮን ብሮች ስጦታ ያህል ነበር ። አንዷን ልጥቀስ፡፡” አሁን እዚህ አዳራሽ ካለነው አብዛኞቻችን ከ30 ዓመት በኋላ በህይወት የለንም ። ከአፈር በታች ነን ። የአንድ ሰው ዕድገት የሀገር ዕድገትን አይገልፅም ። አቅም ያለን ለወጣቶች ሥራ መፍጠር ካልቻልን ትርጉም ያለው ሐብት አይደለም ያፈራነው ።”(© አስቻለው ጌታቸው)

Continue Reading
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top