Connect with us

ለግጭት ምክንያት የነበረው ቦታ ለቤተክርስቲያን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

ለግጭት ምክንያት የነበረው ቦታ ለቤተክርስቲያን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ
Photo : Facebook

ህግና ስርዓት

ለግጭት ምክንያት የነበረው ቦታ ለቤተክርስቲያን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ግጭት ተከስቶበት በነበረበት ቦታ በአዲስ አባባ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቤተክሰስቲያን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ።

በስነ ስርዓቱ ላይ የየክፍለ አገሩ አገር ስብከት መሪዎች፣ ምዕመናንና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡ ስነስርዓት ላይ ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መላከ ኃይለ አባ ወልደ ገብርኤል ነጋሽ እንደተናገሩት፤

የአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር በሀዘናቸውና በደስታቸው ጊዜ ከጎን በመቆም ለችግሩ ፈጣን የሆነ ምላሽ በመስጠቱም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሰላም ለሁሉም አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት የሁሉም እምነት ተከታዮች ችግሩን ለመፍታት ላደረጉት ጥረት አድናተታቸውን ገልጸዋል።

ችግሮች ሲፈጠሩ በመደጋገፍ የመፍታት ባህሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በበኩሉ ከዚህ በፊት የተፈጠረው ችግር ዳግም እንዳይከሰት ቤተክርስቲያን በትኩረት መስራት እንዳለባት አሳስቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በመወከል በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ቤተክርስቲያኗ ልጆቿን በስነ ምግባር ታንፀው አገር ወዳድ እንዲሆኑ የምታደርግ በመሆኗ ድጋፍ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል።

ችግሩ ሊደርስ የቻለው የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ችግሮች በተያዘበት ወቅት መሆኑንም ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ችግር የደረሰው በመንግስት በኩል ለሃይማኖት ቦታ ለመስጠት የተዘጋጀ ደንብና መመሪያ ባለመዘጋጀቱ እንደሆነም ገልፀዋል።

ሌሎች ካርታ የሌላቸው የእምነት ቦታዎች ስላሉ የሃይማኖቱ ተከታዮች በማስተዋልና በማገናዘብ ከመንግስት ጋር በመወያየት ያለውን ችግር መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ‘ህገ-ወጥ’ ግንባታ በሚል ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም ሌሊት ላይ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ታወሳል።

መጋቢት 06/2012 (ኢዜአ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top