Connect with us

ዮሪ ሙሴቬኒ የአፍሪካ መሪዎች ህዳሴዉ ግድብ ላይ የሚመክሩበት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቁ

ዮሪ ሙሴቬኒ የአፍሪካ መሪዎች ህዳሴዉ ግድብ ላይ የሚመክሩበት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቁ
Photo : Facebook

ማህበራዊ

ዮሪ ሙሴቬኒ የአፍሪካ መሪዎች ህዳሴዉ ግድብ ላይ የሚመክሩበት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቁ

የዩጋንዳዉ ፕሬዚደንት ዩሪ ሙሴቬኒ ኢ.ፌ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ በእንቴቤ ተገናኝተዉ መወያየታቸዉን ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በህዳሴዉ ግድብ ላይ እንዲመክሩ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ መጠየቃቸዉ እየተዘገበ ነዉ፡፡

ሙሴቬኒ በአባይ ወንዝ ላይ ያጋጠመዉን ዉጥረት በተመለከተ የአፍሪካ መሪዎች በግልፅ ሊነጋገሩበት የሚያስችል ጉባዔ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ጉባኤዉ ወንዞችን ፍትሃዊና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ በጋራ ለመጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ ላይ አጽዕኖት ሰጥቶ መነጋገር አለበት ብለዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የአባይ ወንዝ ለሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያለዉ ወንዝ መሆኑን ላይ የጋራ ግንዛቤ ላይ መድረሳቸዉንና በተፋሰሱ ሀገራት ዉስጥ የሚገኙ ህዝቦችን ህይወት ለማሻሻልና ሲባል በሀገራቱ መካከል የሚፈጠሩ ቅራኔዎች በአፍሪካዊያን አፍሪካዊ መፍትሄ ሊበጅላቸዉ እንደሚገባ መግባባት ላይ መድረሳቸዉም ተገልጧል፡፡

ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ትልቁ ግድብ የሚሆነዉን የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ዙሪያ ኢትዮጲያ፤ግብፅና ሱዳን ያካሄዷቸዉ ስምምነቶች ፍሬ ማፍራት ሳይችሉ አመታት አስቆጥረዋል፡፡ ኢትዮጲያ የግድቡ አሞላልና ዉሃ አለቃቅን በተመለከተ በአሜሪካን ጣልቃገብነት ሲካሄድ የነበረዉ ድርድር ብሄራዊ ጥቅሜን የሚጎዳ ነዉ በማለት ከድርድሩ ራሷን ማግለሏና የግድቡም የግንባታ ሂደት በተያዘለት መርሀ ግብር እንደሚቀጥል ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top