Connect with us

ወዴት እየሄድን ነው? ስግብግብ ነጋዴና ስስታም ደንበኛ

ወዴት እየሄድን ነው? ስግብግብ ነጋዴና ስስታም ደንበኛ
Photo : Facebook

ህግና ስርዓት

ወዴት እየሄድን ነው? ስግብግብ ነጋዴና ስስታም ደንበኛ

ስግብግብ ነጋዴና ስስታም ደንበኛ፤
ከሞት በሚያተርፍ የሀገር ልጅ እምነት ስለሌለኝ ለኢትዮጵያ መቼም ነጻ ገበያ አልመኝም፡፡ / (ከስናፍቅሽ አዲስ)

ታመህ ተኝተህ መትረፍህ መክሰር የሚሆንበት የሬሳ ሳጥን ሻጭ፣ ወረርሺኝ ኑሮውን መቀየሪያ የሚመስለው ባለ ፋርማሲ፣ ከመኪና በመጋጨትህ የሚያስማማ መሳይ ደስተኛ ትራፊክ፣ ተጠርጥረህ ፖሊስ መዳፍ ስትገባ አገኘሁት የሚል መለዮ ለባሽ ምን አለፋን ሁሉ በሌላው መከራ ባለጊዜ የሚሆንበትን እድል ብቻ የሚያስብበት፤

ኮረና ገባ ሲባል ከመሳቀቅ ከማስክ ትርፍ ብር ለማጋበስ ከዜናው እኩል ገንዘብ የሚያንር ስግብግብ ነጋዴ አየን፤ ነጭ ሽንኩረት መድሃኒት ነው ሲባል ጠዋት በሸጠበት ዋጋ ከሰዓት እንቢ የሚል አጋጠመን፣ ጸረ ጀርም የቅድሙን ስጠኝ ስትሉት ጨምሯል ባይ ተመለከትን፡፡

ወዴት እየሄድን ነው?
ይሄ ለመተዛዘብ የመጀመሪያችን አይደለም ብዙ ተያይተናል ብዙ ተጎዳድተናል፡፡ ዛሬም ግን በሞት ማትረፍ ከሚሻ ስግብግብ ነጋዴ ጋር ስስታም ደንበኛው ሆነን አለን፤ አንድ ማስክ ሲበቃው መጠባበቂያ አስር ሊገዛ የሚፈልግ ስስታም ወትሮም ከርሱን ብቻ ከሚያስበው ነጋዴ ጋር ሲገናኝ የሚሆነውን አስቡት፤

ለዚህ ነው ነጻ ገበያ የማያስፈልገን ለዚህ ነው እንዲህ ላሉ ነጋዴዎች የጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማርያም ያለ መሪ የሚያስፈልጋቸው ምክንያቱም በሞት የሚያተርፍ ከማትረፉ በፊት መሞት አለበትና፤

ምን ቢጨክን ዓለም ጎረቤቱን ጀሶ ጋግሮ አያበላም፤ የአይጥ ዱለት አያቀርብም፣ ሸክላ ፈጭቶ በርበሬ አይልም፤ ዓለም ሩቅ ባለና በማያውቀው ዓለም ለመጨከን ሲቸገር እኛ ግን ጎረቤታችንን እንጨክንበታለን ምክንያቱም ከሞት ማትረፍ ነውር አይደለምና፤

ዛሬ በዚህ አስደንጋጭ ስሜት ውስጥ ሆነን ኪሳቸውንና ኑሯቸውን የሚቀይሩ የመሰላቸው ክፉዎች ከዚህ የባሰ ሊያደርጉ የሚችሉበትን አንጀት የሚያጡ አይደሉም፡፡ አንዳችን ግን ልናስቆመው ይገባል፡፡ ስስታም ደንበኛ አለመሆንና ስለሚበቃን ብቻ ማሰብ የገብጋባውን ነጋዴ የሻርክ አፍ ይዘጋዋልና፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top