የዳንኤልን ሚዛናዊነት ተጠራጣሪ ተቃዋሚ ጉዳይ | ከሰለሞን ሃይሉ
ትናንት የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የፕሬስ ቦርድ አባልነት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ አስመልክቶ የሁለት ጎራ ሙግት ስመለከት በእጅጉ ተገርሜያለሁ፡፡ የዳንኤል ደጋፊዎች ስለ ዳንኤል ብቃትና አቅም ሲናገሩ የእኛ ስለሆነ ምንም አታመጡም የሚል ይዘት ያለው ዳንኤልን የሚያክል ለሀገር የሚሆን ሰው ወደ አንድ ጎራ የመሰብሰቡ ሀሳብ የማይጠቅም መስሎ ተሰምቶኛል፡፡ የዳንኤል ችግር የቱ ነው ብሎ የዳንኤልን አቅም ማሳየትና የጋራ ሊሆኑ የሚገባቸው ሰዎች የጋራ አድርጎ ሀገር የመስራቱ ባህል መዳበር አለበት፡፡
በሌላ በኩል ሌላው አጠራጣሪ ጉዳይ የዳንኤል ክብረት ደጋፊዎች የተምታታ ሀሳብ ነው፡፡ ዳንኤል ሊቅ ነው፤ ዳንኤል ይችላል ብሎ የሚሟገት ደጋፊ ዳንኤል ዶክተር አብይ ይችላል ያለውን ምክር ለምን መስማት አልፈለገም? በውኑ ዳንኤልን ወዶ የሚያማክረውን መሪ ጠላት ማለት ይቻላልን?
ዶክተር አብይ ውሸታም ነው እያሉ ዳንኤል የእኛ ልጅ ኦርቶዶክሱ ከተባለ ዳንኤል አብይን እናግዘው ሲል የውሸት ደጋፊ ሆኖ ነውን? ጉዳዩ የዳንኤል ደጋፊዎች ብዙዎቹ በዳንኤል ድጋፍ ሊያበሽቁት የፈለጉት ሃይል አለ ብለው ስላቀዱ ነው፡፡
የዳንኤልን ሹመት የተጠራጠሩት የፓርላማ አባላትና ይሄንን የደገፉት ጸረ ዳንኤል ሰዎችስ ከዚህ ቀደም አቶ ጌታቸው ረዳ ዳንኤል ክብረትን ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አድርጎ ሲሾመው ያልተቃወሙት ለምን ነበር?
ያኔ ዳንኤል ክብረት ሀገሩን ለማገልገል የፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነትን ሲሾም ከወያኔ ጋር ሰራ ብለው ያጉረመረሙት ዛሬ ከዚህ በላይ ይገባዋል ብለው ደጋፊዎቹ የሆኑት ከስካር ፖለቲካ ስላልወጣን ነው፡፡ የዳንኤልን ተቃውሞ ሃይማኖታዊ አናድርገው ምክንያቱም ዳንኤል በአክራሪ የትግራይ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችም ዘንድ ተመሳሳይ ቅሬታዎች ያሉበት ሰው ነው፡፡
የፓርላማው ውሎ ራሳችንን ብንመለከትበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ለምን የጋራ ምልክቶች የሆነ ግለሰቦችን ዘውግ እናስይዛቸዋለን፡፡ በዲያቆን ዳንኤል አይነት ግለሰቦች የምንስማማበት ብዙ ነጥብ ኖሮ የምንለያየበት እንዲሰፋ ማድረግ ሰው የለሽ ያደርገናል፡፡
ከነችግራቸውም ቢሆን የዳንኤል አይነት ሰዎች የጋራችን ሆነው ቢቀጥሉ እንጠቀማለን፡፡ እነሱም ከስህተታቸው ተምረው የወል ምልክት የሚሆኑት ስንገፋቸውና ተገፉ ብለን ነጥለን የእኛ ስናደርጋቸው አይደለም፡፡ የራሳችን ክልል የራሳችን ምሁር የራሳችን ጳጳስ የራሳችን ፓስተር እያልን ከቀጠልን የጋራ አገር እንዴት ይኖረናል፡፡ እናም ከጋጋታ ይልቅ ቆም ብለን መበሻሸቁን ብንተወው፤