Connect with us

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኘረስ ቦርድ አባልነት ሹመት አወዛገበ

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኘረስ ቦርድ አባልነት ሹመት አወዛገበ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኘረስ ቦርድ አባልነት ሹመት አወዛገበ

#ሹመት
የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኘረስ ቦርድ አባልነት ሹመት አወዛገበ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአራት ሚኒስትሮች እና የአንድ ኮሚሽነር እንዲሁም የኢትዮጵያ ኘረስ ድርጅት ዘጠኝ የቦርድ አባላት ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ተወያይቶ አፅድቋል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

1. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡- ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፤
2. አቶ ላቀ አያሌው፡- የገቢዎች ሚኒስትር፤
3. ዶክተር ሊያ ታደሠ፡- የጤና ጥበቃ ሚኒስትር፤
4. ወ/ሮ ፊንሰን አብዱላሒ፡- የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው በ21 ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምፅ ፀድቆ ተሹመዋል፡፡

ከዚህ ሌላ አቶ ፀጋዬ አራጌ የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ሹመት በ11 ተቃውሞ፣ በስድስት ድምፀ-ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ኘረስ ድርጅት ዘጠኝ የቦርድ አባላት በጠ/ሚኒስትሩ አቅራቢነት ፓርላማው በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
በዚህ መሰረት አቶ አወሉ አብዲ ሰብሳቢ፣ ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ፣ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣አቶ ማንያዘዋል እንደሻው፣ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ዶ/ር ወዳጄህ፣ ዶ/ር ኮንቴ፣ ወ/ሮ አበበች፣ አቶጌትነት ታደሰ ፀሀፊ ናቸው።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሀይማኖት ውግንና የያዙ ንግግሮች አድርገዋል በሚል የቦርድ አባልነት ሹመታቸው በአንዳንድ የም/ቤት አባላት ጥያቄ መነሳቱን ተከትሎ አፈጉባኤው በተለየ ድምፅ እንዲሰጥ አድርገዋል። በዚህ መሰረት 146 ድጋፍ፣ 129 ተቃውሞ፣ 27 ተአቅቦ የተቆጠረ ቢሆንም በአባላቱ ዘንድ የቆጠራ ስህተት አለ በሚል በቀረበው ቅሬታ መሰረት በድጋሚ እንዲቆጠር ተደርጎ 148 ድጋፍ፣ 126 ተቃውሞ፣ 24 ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ መፅደቁን አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀዋል።በተመሳሳይ ሁኔታ በሎሎቹ የቦርድ አባላት ድምፅ ተሰጥቷል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top