Connect with us

ወይዘሮ ነፃነት አስፋው እና የቀድሞ የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ወይዘሮ ነፃነት አስፋው እና የቀድሞ የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ማህበራዊ

ወይዘሮ ነፃነት አስፋው እና የቀድሞ የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን እና በተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊነቶች ላይ ያገለገሉት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ወይዘሮ ነፃነት ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ፣ የኢፌዴሪ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዲኤታ እና በሌሎች የስራ ሀላፊነቶች ላይ ሰርተዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ውስጥም የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ሻለቃ በፍቃዱ ቶሌራ ባደረባቸው ህመም ህክምናቸውን በሀገር ውስጥና በውጪ ሲከታተሉ ቆይተው የካቲት 29 ቀን 2012 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ኮሚሽነር በፍቃዱ ቶሌራ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ከማገልገላቸው በተጨማሪ በኮሚሽኑ ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች በስራ ኃላፊነት ሰርተዋል፡፡ኮሚሽነር በፍቃዱ ቶሌራ ከመጋቢት 9 ቀን 1997 ዓ/ም ጀምሮ ህዳር 28 ቀን 2002 ዓ/ም በክብር በጡረታ እስከ ተሰናበቱበት ወደ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተዛውረው አገልግለዋል፡፡

በፍቃዱ ቶሌራ ከፖሊሳዊ ተግባራቸው ጎን ለጎን በልዩ ልዩ መንግስታዊና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሰርተዋል። የኮሚሽነር በፍቃዱ ቶሌራ የቀብር ነ-ሥርዓት መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ ወ-ጳውሎስ የሚፈፀም ይሆናል፡፡(ምንጭ:-ፋና እና አ/አ ፖሊስ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top