Connect with us

“እንኳን ለመሬቷ ለጭብጥ አፈሯም ቢኾን ስሱ ነኝ፡፡”

"እንኳን ለመሬቷ ለጭብጥ አፈሯም ቢኾን ስሱ ነኝ፡፡"

ባህልና ታሪክ

“እንኳን ለመሬቷ ለጭብጥ አፈሯም ቢኾን ስሱ ነኝ፡፡”

“እንኳን ለመሬቷ ለጭብጥ አፈሯም ቢኾን ስሱ ነኝ፡፡”
አንገቱን የሰጠው ንጉሳችን ዩሐንስ 4ኛ
****
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የታላቁን ንጉሥ የዐፄ ዩሐንስ አራተኛን የመስዕዋትነት መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ ታላቁን ንጉሥ የዘከረበትን ጽሑፍ ጀምሯል፡፡ መልካም ንባብ፤ | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ንጉሳችን ዮሐንስ እንለዋለን፤ እሱ ራሱን የጽዮን ንጉሥ ይላል፡፡ ሀገሩን የሚወድ ለምድሩ የሚጨነቅ ስሱ ነው፡፡ ደግሞ በፌዴራሊዝም ያምናል፤ እሱ ንጉሠ ነገሥት ኾኖ ለምኒልክ በሸዋ መንገስን፣ ለንጉሥ ሚካኤል ንጉሠ ወሎ መኾንን ደግሞም ለአዳል ተክለሃይማኖት የጎጃም ንግስናን የሰጠ ነበር፡፡

ጥር በገባ በአስራ ሦስተኛው ቀን በ1864 ዓ.ም. ቀኑ ሰንበት ሳለ በርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም አትናቴዎስ በተባሉት ጳጳስ እጅ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ተብሎ ነገሠ፡፡ ከዚህስ በኋላ ንጉሣችን ነግሷልና አንቱ እል ዘንድ የአባቶቻችን ህግ ያስገድደኛል፡፡

ንጉሡ ዩሐንስ አራተኛ በዚህ ቀን የንግሥና በዓላቸውን አድምው አከበሩ፤ ሦስት ቀን ሙሉ ድግስ ኾነ፡፡ አራት ሺህ ድልብ ሰንጋዎች ተጣሉ፡፡ የጠጁ ብዛት ከመቶ ሺህ በላይ እንስራ ነበር፡፡

ዐፄ ዩሐንስ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የደከሙ ንጉሥ ናቸው፡፡ ምንፍስናው ቢጫናቸውም በድንበር በሀገር ፍቅርና በሉዓላዊነት አይታሙም፡፡ ደጃዝማች ሳሉ ካሳ የሚለው ስም ገናና ነበር፡፡ በአድዋ ግዛት የተወለዱት ካሳ ከተንቤን ባላባት የተገኙ ንጉሥ ነበሩ፡፡

ሀገርን አንድ አድርጎ የመግዛት ምኞታቸው ማዕከላዊት ካከበረ የአካባቢ መስፍን አላጋጫቸውም፡፡ ስኬታማ የሚባል የእረፍት ዘመን አልነበራቸውም፡፡ ይልቁንም የድንበር ወረራ ትንኮሳዎች እረፍት ያሳጧቸው መሪ ናቸው፡፡

ይወደዳሉ፤ በተለይም በመጨረሻዋ ሰዓት ለሀገራቸው መከበርና መታፈር ራስን የመስጠት ፍቅራቸው አስከብሯቸዋል፡፡ ለዚህም ነው፤
“በጎንደር መተኮስ
በደንብያ መታረድ አዝኖ ዮሐንስ
ደሙን አፈሰሰ እንደ ክርስቶስ” የተባለላቸው፡፡ ጎንደር ስትጣራ አቤት ያሉትን ንጉሥ እስከ መተማ ዩሐንስ ዘልቀን ስማቸውን ከፍ እናደርጋለን፤ ታሪካቸውን ስለ ሀገር ድንበር በከፈሉት ዋጋ ተንበርክከን ክብር ሰጥተን እንዘክራለን፤ ንጉሣችን ዩሐንስ እንላለን፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top