Connect with us

ጎመን በጤና

ጎመን በጤና
Photo: Facebook

ጤና

ጎመን በጤና

“ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ይሉሃል ይህ ነው፡፡ ዓለምን እያተራመሰ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ሠላምታን በሩቁ ማድረግ አንድ የጥንቃቄ መንገድ ነው፡፡

የኮሮና ቫይረስ በቻይና ውሃን ከተማ ተቀስቅሶ አስከ ዛሬ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ብቻ 109 አገራትን አዳርሷል፡፡ 110 ሺ በቫይረሱ ሲያዙ 3 ሺ 831 ሰዎች ሞተዋል፡፡ 62 ሺ 356 ገደማ ተገቢውን ሕክምና አግኝተው አገግመዋል ተብሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ -19) ስርጭት

በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለ የዝግጅት ሁኔታ

• በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች አራት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ (467,280) በሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡

• በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት (277,977) በሙቀት መለያ ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ስምንት (6,858) በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡

• በሽታውን ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት የመጡ ተጓዞች የጤና መረጃ ቅጽ ከመሙላታቸው በተጨማሪ ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የሚደረግ የጤና ክትትል ተደርጎላቸው ያጠናቀቁ አንድ ሺህ ዘጠና ሶስት (1093) ክትትል ተደርጎላቸው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንድ ሺህ ሃያ አንድ (1021) የሚሆኑት ደግሞ የጤና ክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

• ከጥር 15/2012 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሰላሳ ሁለት (32) የበሽታው ተመሳሳይ ምልክቶች በማሳየታቸው እና በሽታውን ሪፖርት ያደረጉ አገራት የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ስለሆነ በተለያየ ጊዜ በለይቶ መቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት አንድ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ሆኖ የለቦራቶሪ ምርመራ ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

• የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን የኢንስቲትዩቱን የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከልን፣ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በሽታውን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን እና የየካ ኮተቤ ለይቶ ማቆያን ጎብኝተዋል፡፡

• ለቴክኖ ሞባይል ሰራተኞች እና ለሄንከን ቢራ ፋብሪካ የጤና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን ለለቡ ባቡር ጣቢያ ሀላፊዎች ደግሞ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

• ዩኒሴፍ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ዝግጅት እና መከላከል የሚውል የኢንፌክሽን መከላከያ ኬሚካል (በረኪና) ለግሷል፡፡

• የተጠናከረ የማሕበረሰብ ንቅናቄ ለመጀመር ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

ሕብረተሰቡ ከዚህ በፊት ማንኛውንም በሽታ ለመከላከል ሲጠቀምባቸው የነበረውን የበሽታ መከላከያ መንገዶች ችላ ሳይል አጠናክሮ እንዲቀጥል እንመክራለን፡፡

ማለትም

• የእጅ ንጽህና በውሃ እና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ

• ለእጅ ንጽህና መጠበቂያ የሚሰሩ አልኮል ነክ ምርቶችን አዘውትሮ መጠቀም

• ባልታጠበ እጅ አይን፤ አፍንጫ እና አፍን አለመንካት

• ቫይረሱን ሪፖርት ከተደረገባቸው አገሮች የመጡ ተጓዦች ሆነው የበሽታውን ምልክት ከሚያሰዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ በተጫማሪም ከ 1-2 ሜትር ርቀት መጠበቅ

• ስለበሽታው በቂ መረጃ በማግኘት መተግበር ይገኙበታል፡፡

የኮቪድ-19 በሽታ አሳሳቢ ደረጃ በደረሰበት በዚህ ጊዜ በተለይም ማኛውም ህመም ያለባችሁ ተጓዦች በሽታው ሪፖርት ወደ አደረጉ አገራት የምታደርጓቸውን ጉዞዎች ወይም በተለያዩ ዘርፎቸ በሽታው ካለባቸው ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ እዲገቡ የምታደርጉ አካላት ጉዞውን እንድታዘገዩ ቢቻል እንድታቋርጡ ይመከራል፡፡ ማንኛውም ተጓዦች በምትሄዱበት ሀገራት ሁሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ካለባቸው አገሮች የመጡ ከሆነ

• በአገራችን መግቢያ እና መውጫ ቦታዎች የሚደረገውን የልየታ አገልግሎት ማግኘትዎን ያረጋግጡ

• ስለነበርዎት ጉዞ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ስለሚጠቀሙት አድራሻ መስጠቶን አይዘንጉ

• እራስዎን ከሌሎች ሰዎች እና ከቤተሰብ አባላት ለ14 ቀናት በማግለል ጤናዎን ይከታተሉ!

• በየዕለቱ የጤናዎትን ሁኔታ ለመከታተል ለሚደውሉ ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ይተባበሩ!

• ትኩሳት፣ ሳልና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመዎት ላስቸኳይ የህክምና እርዳታ 8335 ይደውሉ፤

• በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎትን ክንድዎን በማጠፍ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ፤ እጅዎን በሳሙናና በውሃ ይታጠቡ!

ትኩረት መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

• የኮሮና ቫይረስ በሽታ ነጭ ጥቁር የቆዳ ቀለም ሳይለይ ሁሉንም የሰው ዘር የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡

• አስካሁን የተረጋገጠ መድሐኒት ወይም ክትባት የሌለው በመሆኑ ሕብረተሰቡ ይህንን በመረዳት እና የጥንቃቄ መንገዶችን በማወቅ እንዲሁም በመተግበር በሽታውን መከላከል ይኖርበታል፡፡

• በተጨማሪም ህብረተሰቡ በሀገራችን እስከ አሁን በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አለመኖሩን አውቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ ኢንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡

• በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሀገራት የሚመጡ ሰዎች አራሳቸን ለ 14 ቀን በመለየት በበሽታው አለመያዛቸውን ሲያረጋግጡ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀለቀሉ እንመክራለን

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የካቲት 29/2012

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top