Connect with us

የህዳሴ ግድብ የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ ነው!

የህዳሴ ግድብ የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ ነው!
Photo: Reuters

ባህልና ታሪክ

የህዳሴ ግድብ የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ ነው!

የህዳሴ ግድብ የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ ነው!
(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ግብጽ በአሜሪካና በአለም ባንክ የተገመደለላትን ፍርድ በአረብ ሊግ ድጋፍ እንዲቸረው አድርጋለች፤ ይህ የሚጠበቅ ነው፡፡ ግብጽ አሜሪካንንም ድጋፍ ማግኘቷም አይገርም፡፡ ከአሜሪካን ጀርባ እስራኤል አለች፤ ኢትዮጵያ የግብጽንና የእስራኤልን ቅራኔ ለማለስለስ በአሜሪካ የቀረበች ጭዳ ናት፡፡ ሱዳንም የአሜሪካንን ልብ ለማራራትና የተጣለባትን ማእቀብ ለማስነሳት፣ ልግስናዋንም ለማግኘት ኢትዮጵያንና አልበሽርን አሳልፋ ሰጥታለች፡፡ የአለማችን ሁለንተናዊ ህልውና ይህ ነው – ከራስ በላይ ንፋስ!

ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የሰጣትን በረከት፣ በስምምነት ፈርማ መስጠት የለባትም፡፡ ይህን ማድረግ የእትዮጵያን ሉአላዊነት እስከወዲያኛው አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር የባህር በር፣ አንድ ሜትር ሳናስቀር በስምምነት ተሰጥቷል፡፡ አባይም የዚያ እጣ እንዳይደርሰው መንግስት መጠንቀቅ አለበት፡፡

ለሀገራችን ሉአላዊነትና ለሰብአዊ ልእልናችን ስንል በአባይ ላይ ያለንን መብት ለማስከበር የሚጠይቀውን ሁሉ (ከማስተዋል እስከ ህይወት) ለመክፈል መዘጋጀት አለብን፡፡ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና በተያዘለት ጊዜ ውሀ መሞላት የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ፣ ከግብጽ ተጽእኖ መውጫ መንገድ ነው፡፡ በአባይ ላይ ያለውንም የሀይል አሰላለፍ እጅጉን ይቀይራል፡፡ . . . በመሆኑም ‹‹የፍጻሜው ጦርነት ነው!›› የግብጾች መዝሙር ቢሆን እንኳን (ይሆናል ብዬ አልጠብቅም)፣ በመንፈስም በጉልበትም መዘጋጀት አለብን፡፡ . . . በአባይ ጉዳይ፣ በሀገር ጉዳይ፣ . . . . በሉአላዊነታችን ጉዳይ ልዩነታችን ዜሮ ሊሆን ይገባል፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top