Connect with us

124ኛው የአድዋ ድል በአል በታንዛኒያ ተከበረ

124ኛው የአድዋ ድል በአል በታንዛኒያ ተከበረ
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

124ኛው የአድዋ ድል በአል በታንዛኒያ ተከበረ

124ኛው የአድዋ ድል በአል በዳሬሰላም የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ባዘጋጀው ፕሮግራም የካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ተከብሮ ውሏል።

በክብረ በአሉ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ፓላማጋምባ ጆን አይዳን ምዋልኮ ካቡዲን ጨምሮ በርካታ የታንዛኒያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ መቀመጫቸውን በታንዛኒያ ያደረጉ አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ የንግድ ማህበረሰብ አባላት፣ ቱር ኦፕሬተሮች፣ የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የወዳጅነት ማህበር አባላት፣ በታንዛኒያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሌሎች ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ካቡዲ በክብረ በአሉ ላይ ባሰሙት ንግግር የአድዋ ድል በአል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካውያን ብሎም በመላው አለም ለሚገኙ ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት የሆነ በመሆኑ የሁላችንም በአል ነው ያሉ ሲሆን፤ በዚህ አጋጣሚ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በዝግጅቱ ላይ የአገራችንን ባህል እና ታሪክ፣ የቱሪዝም መስህብ እንዲሁም የኢንቨስትመንት እና ንግድ አማራጮች ቀርበው በስፋት የተዋወቁ ሲሆን በታንዛኒያ አገር ያሉ በርካታ የህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።

ምንጭ፡- በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top