Connect with us

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ቤታቸውን መረከብ አልቻሉም

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ቤታቸውን መረከብ አልቻሉም
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ቤታቸውን መረከብ አልቻሉም

ከቤቶች መካከል አንደኛው ብሎክ ለመንግሥት ባለሥልጣናት ተላልፎ ተሰጥቷል

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዕድለኞች እጣው ወጥቶ ውል ተዋውለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቆጣቢዎች እስካሁን ወደ መኖሪያ ቤታቸው መግባት አለመቻላቸው ታውቋል፡፡

መገነኛ፤ ከገቢዎች ሚንስቴር አጠገብ የሚገኘው የ40/60 የጋራ መኖሪያ መንደር በሎክ ሦስት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ተሰጥቷል፡፡ ሕንፃው ቀለም ተቀብቶ፣የውሃና መብራት መሰረተ ልማት አውታሮች ተዘርግተውለት ለባለሥልጣናቱ መደበኛ አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡

ግቢው ውስጥ የባለሥልጣናቱ የመኪና ማቆሚያ የተዘጋጀ ሲሆን ተሸከርካሪዎች ሲወጡና ሲገቡም ይስተዋላል፡፡ ‹‹ከዛሬ ነገ መንግሥት ወደ ቤታችን እንድንገባ ጥሪ ያቀርብልናል ስንል ቤታችን ውስጥ ራሳቸው ባለሥልጣናቱ ገብተውበታል›› ብለዋል የኢትዮጲስ የመረጃ ምንጮች፡፡ ለባለሥልጣናቱ ደህንነት ሲባል ግቢው በፍርግርግ ብረት ታጥሮ እና ጥቁር ቀለም ተቀብቶ እየተገለገሉበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

‹‹ከ18 ሺህ በላይ የ40/60 ቆጣቢ እድለኞች ችላ ተብለው በተለየ መልኩ የዚህ ሕንፃ ብሎክ 3 ኗሪዎች ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ወሳኝ ኩነት ፅህፈት ቤት በመሄድም የቀበሌ መታወቂያ እያወጡ ነው፡፡ እዚያው ግቢ ውስጥ እና ከግቢው ውጭ የሚገኙ ሌሎች ሕንፃዎች ተጠናቀው ለእድለኞች ሳይተላለፉ የብሎክ ሶስት ብቻ መጠናቀቅና ለባለሥልጣናት መሰጠቱ አስገራሚ ነው፡፡›› ብለዋል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢትዮጲስ የመረጃ ምንጮች፡፡

(ምንጭ፡-ኢትዮጲስ ጋዜጣ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top